በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስአሃዱ አምላክ አሜን።
ሐምሌ ፪ቀን ፪ሺ፲ ዓ/ ም JULY 9, 2018
ለክቡር ጠ/ሚ/ዶ/ር/ ዓብይ አህመድ፤ ለኢ/ ኦ/ ተ/ሕዝበ ክርስቲያንና ለአገር ወዳድ በሙሉ
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያውጪ በዶ/ር ዓብይ እና በጓደኞቻቸው አማካኝነትእየተደረገ ያለውን በጎ የሆነ ለውጥ በጽኑ የምንደገፍመሆናችንን አስቀድመን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን።በመቀጠልም ቀጥታ ወደ ወቅታዊና እኛንም ሆንብዙዎችን በብርቱ ወደ አሳሰበን ጉዳይ ስናቀና፦
ሀ/ እርቀ ሰላም እንዲወርድና ሕዝበ ሙስሊሙንየሚወክል መጅሊስ እንዲቋቋም እየተደረገእንደሚገኘው ሁሉ በኢ/ ኦ/ ተ/ ቤተክርስቲያንም እርቀሰላም እንዲወርድ የተጀመረው እንደተጠበቀ ሆኖለወደፊትም በማያዳግም ሁኔታ ቀኖና ወይም ሕገቤተክርስቲያን በሚፈቅደውና በሚያዘው መሰረትመንበሩ ለሚገባው አባት ተሰጥቶ የቅዱስ ሲኖዶስአንድነት እንዲጸናልን?
ለ/ በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በኩል የሚገኘውጥንታዊው የማሕበረ ሥላሴ ገዳም እና በአካባቢውበሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሱዳን ወታደሮችየሚያደርሱት ወረራና ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም?
ሐ/ የላመና የጣመውን የሥጋ ፈቃድ ሁሉ ከመናቅጀምሮ እጅግ መራራ የሆነውን የቋርፍ ተክል በቀንአንድ ጊዜ ብቻ እየቀመሱ ከኢትዮጵያ አልፈው ለዓለምሁሉ የሚጸልዩ ገዳማውያን የዋልድባ አባቶች እናእናቶቻችን እንዲሁም በገዳሙ ላይ የተጀመረው ጥፋትእንዲቆም ይህም በቅርቡ ከእስር ከተፈቱት ከእነ አባገብረኢየሱስ ኪዳነማርያም ጀምሮ ጥቃቱ በሦስቱምየዋልድባ ገዳማውያን ላይ እየተፈጸመ የሚገኝ ሲሆንበተለይ ግን በዋልድባ አብረታንት ገዳማውያን ላይእየተደረገባቸው የሚገኘው ግን ከሁሉም የከፋከመሆኑም ባሻገር እስካሁን ገዳማውያውኑ ተሰደውበመከራተት ላይ ስለሆኑ በተቻለ ፍጥነት ወደገዳማቸው እንዲመለሱልን ለጥፋት ተልዕኮ ከአበመኔትእና ዕቃ ቤት ጀምሮ በህ/ ወ/ ሓ/ ት/ ተመልምለው ወደየገዳማቱ የገቡ በርካታ ሰዎች በአስቸኳይ ገዳሙቹንለቀው እንዲወጡ እንዲደረግልን?
መ/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የጥምቀትናየመስቀል ደመራ ማክበሪያዎችና ሌሎችም ቦታዎችከቤተክርስቲያኗ ላይ በጉልበት እየተነጠቁ ለሌሎችየተሰጡባት ቦታዎች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተክርስቲያን እንዲመለሱላት?
ሠ/ የቤተክርስቲያናችንና የአገር አንጡራ ሃብትየሆነውን በብዙ ቢሊየን የሚቆጠረውን ገንዘብከቤተክርስቲያን ዓላማ ውጪ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስንመሳርያ በማድረግ ህ/ ወ/ ሓ/ ት/ በአብዛኛው አንድን ጎሳብቻ ተጠቃሚ ለማድርግ የባንክ ሂሳብ (አካውንት)ተከፍቶ በብዙ ቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብተመዝብረናልና ይህም እንዲመለስልን?
ረ/ ቀደም ሲል ህ/ ወ/ ሓ/ ት/ ካሕናትን እየመለመልና የስልጣን መጠብቂያ መሳሪያ እንዲሆኑ በማሰልጠን ክህነት የሌላቸውን ደግሞ እየመለመለና ስልጠና በመስጠት ከገብያ ላይ የመነኩሴ ቆብና ቀሚስ እየገዛ በየገዳማቱና አድባራቱ በመሰግሰግ የየገዳማቱ አበመኔትና እመመኔት ያደረጋቸውን ሁሉ እንዲያነሳልን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመብንን ሁሉ ከቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ እንዲያስወጣልን ከዚህ ጋር በተያያዘም በሙስናና በአብዛኛው አንድን ጎሳ ብቻ ተጠቃሚ ለማድረግ በታቀደ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከቤተ ክህነት እስከ ወረዳ ቤተክርስቲያን ተደራጅተው ቤተክርስቲያናችንንና አግራችንን የሚዘርፉ ግብረበላዎች እንዲወገዱልን? በአጠቃላይ ህ/ ወ/ ሓ/ ት/በሁሉም ቤተዕመነቶች ላይ በተለይም በኢ/ ኦ/ ተ/ቤተክርስቲያን ላይ የጫነውን እጁን ሙሉ ለሙሉ እንዲያነሳልን?
ሰ/ እግዚአብሔር በጥፋት ውሃ ዘመን ለሃጋራችንለኢትዮጵያ የሰጠንን ባንዲራችን ላይ የሰይጣን ዓርማ የሆነው የ ፮ ፮ ፮ (666) ዓርማና ኮከብ በሰንደቅ ዓላማችን ላይ መደረጉ አልፎ ተረፎም በሕንጻቤተክርስቲያን ላይ መደረጉ በእጅጉ አገራችንን፣ ህሊናችንን እና ሃይማኖታችንን እየጎዳው በመሆኑ ይህየሰይጣን ዓርማ የሆነ ኮከብ ከሰንደቅ ዓላማችን ላይእንዲነሳልን?
ሸ/ ኢትዮጵያ አገራችን የተቀደሰችና ለብዙ ሺዓመታትም መንፈሳዊና ሌሎች ዕሴቶቿን ጠብቃ የኖረችአገር ሆና ሳለ ባለፉት የቅርብ ዓመታት ግን ሰዶማዊነትወይም የተማሳሳይ ጾታ የወሲብ ግንኙነት በአገራችንላይ እንደ ወረርሽኝ እየተፈጸመብን መሆኑ የአደባባይሚስጥር መሆን ከጀመረ ቆይቷል። ይህም ሕጻናትወንዶችና ሴቶችን በተለይም ምስኪን የጎዳና ተዳዳሪወግኖቻችን ላይ በስፋት እየተፈጸመብን የሚገኝአስከፊና አጸያፊ ሰቆቃ ሲሆን ድህነታችንን እንደመሳሪያ በመጠቀም ይህንን እርኩሰት በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድንቀብል ከሚደረግብንተጽዕኖ ጀምሮ ሕጻናትን በመደለልና በማባበል እየሸጡ የደላላና የአመንዝራ ባለሃብቶች የወሲብ ሰለባ የሆኑዜጎቻችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ይገኛል። ስለዚህ ይህ አስከፊና አጸያፊ ወረርሽኝ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያስቆምልንና ለችግሩ ሰለባዎችም የአካልና የስነልቦና ትምህርት የሚሰጥ የሕክምና አካል በአስቸኳይ ተቋቁሞ ወገኖቻቸንንና አግራችንን እንድንታደግ በአክብሮት እንጠይቃለን?
ቀ/ በእስራኤል ውስጥ የሚገኙት እና ጥንታውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ያቆዩልን እንደ ዴር ሡልጣንና ሌሎችም ቅዱሳን ገዳማትና አድባራት በግብጻውያን ወረራ እየተፈጸመባቸው ከመገኘቱም ባሻገርገ ዳማቱንም እንዳናድስና የኤሌክትሪክ መብራትናየመጸዳጃ አገልግሎት በራሳችን ይዞታ ላይ እንዳንጠቀም ለዘመናት ስለተከለከልን ይህም ታውቆ የኢትዮጵያ መንግስት ከእስራኤል መንግስት ጋርበመነጋገር በእስራኤል የሚገኙ ገዳማትና አድባርት ይዞታዎቻችንና መብቶቻቸውን እንዲያስከብርልን እየጠየቅን የእስራኤል መንግስት ለሬዲዮ ጣቢያነት የሚገለገልበትን ሕንጻችንን ግብጾች እንደለመዱትሊቀሙን በእስራኤል ፍርድ ቤት ቢሞግቱንም በቅርቡፍርድ ቤቱ በቀረበለት ማስረጃ መሰረት የሕንጻውንባለቤትነት ለኢትዮጵያ ማረጋገጡ የሚያስደስት ሆኖ ሳለከአገር ቤት ጀምሮ እስክ ውጪ አገር ድረስ እጁንየዘረጋው የሙስናና የዘረፋ ቡድን ገቢውንእየተቀራመተው ስለሚገኝ አፋጣኝ መፍትሄእንዲሰጥበት በአክብሮት እንጠይቃለን፧
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ቤተክርስቲያናችንን እና አገራችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ መላው ሕዝበክርስቲያንና አገር ወዳድ የሆንን ሁሉ በጋራ እንድንታገል፤ እንደዜጋም አገራችን ከኛ የምትጠብቀውን ሁሉለማድረግ ዝግጁ ሆነን እንድንደመር በአክብሮት እኔናመሰሎቼ እንጠይቃለን። እናመሰግናለን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
/ውብሸት ከበደና መሰሎቹ/