የአዲስ አበባ ም/ቤት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የመዘበሩ ሰዎች ላይ ርምጃ ለመውሰድ...

የአዲስ አበባ ም/ቤት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የመዘበሩ ሰዎች ላይ ርምጃ ለመውሰድ መወሰኑን ገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር የተለያዩ ጉድለቶችን በሪፖርቱ ለከተማው ምክር ቤት ዛሬ አቅርቧል፡፡በሪፖርቱም በለያየ መንገድ የከተማዋ ባልስልጣናት የህዝብ ሀብት እንደዘረፉ በዝርዝር ተገልጿል።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፦

  1. ከደንብና መመሪያ ውጭ የተፈጸመ ግዥ……….…112 ሚሊየን ብር በላይ
  2. በወቅቱ ያልተሰበሰበ……………………..….329 ሚሊዬን ብር በላይ
  3. ጥሬ እቃ ተሰጥቶ ምላሽ ያልተደረገ…………41 ሚሊዬን ብር በላይ
  4. ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ ተከፋይ ሂሳብ….123 ሚሊዬን ብር በላይ
  5. በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ………………137 ሚሊዬን ብር በላይ
  6. ከመመሪያ ውጭ ተከፈለ አበል…………….298 ሺ ብር በላይ
  7. ከውል በላይ ተከፈለ ሂሳብ…………….…….4 ሚሊዬን ብር በላይ
  8. ማስረጃ ሳይቀርብ የተከፈለ………………96 ሺ ብር በላይ
  9. ያለ አግባብ ለተለያየ ህትመት የዋለ…………..13 ሚሊየን ብር በላይ
  10. የስራ ግብር ያልተከፈለበት ክፍያ…………..…840 ሺ ብር
  11. ለፋርማሲ አገልግሎት ተገዝተው ስራ ላይ ያልዋሉ የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች……………11 ሚሊየን በላይ
  12. በቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ በኩል በራሳቸው ስም ለ9 ዩኒቨርሲቲዎች 7000 ቶን ብረት አራት ሚሊዬን ዶላር ወጭ ተደርጎ ቢገዛም ዩኒቨርሲቲዎቹ ስለመረከባቸው  የተገኘ ሰነድ አለመኑ ተገልጿል።

በመሆኑም የከተማው ምክር ቤት ከህግ ውጭ ሀብት ያባከኑና የመንግስት ሀብት በመዘበሩት ላይ ርምጃ ለመውሰድ የውሳኔ ሀሳብ ማፅደቁ ታውቋል።

LEAVE A REPLY