ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተከራይቶ ይኖርበት የነበረውና ሐምሌ 5/2008 ዓም ጥቃት የደረሰበት ቤት ለሕዝብ ሙዝዬም እንዲሆን ሲሰራ ቆይቷል። ንግስት ይርጋና አታላይ ዛፌ ቤቱን ለመግዛት ሲያስተባብሩ ቆይተዋል። በትናንትናው ዕለትም ከቤቱ ባለቤት አብርሃም ገበየሁ ጋር ውል በመፈፀም ለሕዝብ እንዲተላለፍ ተደርጓል።
ቤቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ዋጋ የወጣለት ሲሆን በትናንትናው ዕለት ለባለቤቱ 350,000 ብር ተከፍሏል። ቀሪው እስከ ነሃሴ 5 እንደሚከፈል ውሉ ላይ ተመልክቷል። እስካሁን ቤቱን ለመግዛት በተደረገው ጥረት:_
1) አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ 340,000 ብር
2) ጌቱ አይንግዳ ከእስራኤል 34250 ብር
3)ሶስና ድልነሳው (ወረቄ ታፈረ)13000 ብር
4)ተመሰገን ሰጣርገው (ጃንተከል ሆቴል)
10000 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።
በንግስት ይርጋና በአታላይ ዛፌ ስም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ምንትዋብ ቅርንጫፍ
የባ ደቁ 1000250255717 ማገዝ ይቻላል!
በተመሳሳይ በትግሉ ወቅት መስዋዕት የሆኑትን ቤተሰቦች ለማገዝ የተቋቋመ መረዳጃ ማህበር ያለ ሲሆን የተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን በማድረግ በእዳ የተያዘውን የእነ ሲሳይ ታከለንና የሎቹንም ንብረት ለማስመለስ እየሰራ እንደሆነ ተገልፆአል። ማህበሩ ሂደቶችን ሲጨርስ የሚታገዝበትን መንገድ ለሕዝብ ያሳውቃል ተብሏል። በእዳ የተያዙትን ንብረቶች ለማስለቀቅና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ በርካታ ገንዘብ ስለሚጠይቅ የሕዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ገልፀዋል።
የአማራ ክልላዊ መንግስት ተጎጅዎችን በማገዝና ቤቱን ሙዝዬም እንዲሆን የሚደረገውን ጥረት አግዛለሁ ማለቱ ተሰምቷል።