ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.
ዶ/ር ኣበራ ሞላ
ዋና መሥሪያ ቤቱ ብራይተን ኮሎራዶ የሆነው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ቍጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት የሆነ ኣዲስ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ (ፓተንት) ሚያዝያ ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ማግኘቱን ኣስታወቀ። (https://patents.google.com/patent/US9733724B2/en) ፓተንቱ የተሰጠው ለግኝቱና የኩባንያው ባለቤት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ሲሆን ኩባንያው የእርሳቸውና የባለቤታቸው የሠናይት ከተማ ነው። “ኣብሻ” ሥርዓት በመባል በታወቀው ኣዲስ ዘዴ መጀመሪያ መርገጫ ላይ ያሉት ቀለሞች የሚከተቡት እያንዳንዳቸው በኣንድ መርገጫ ብቻ ሲሆን ሌሎቹ በሁለት መርገጫዎች ነው። ይህም ኮምፕዩተሮች፣ የእጅ ስልኮችና ተመሳሳይ መሣሪያዎች ውስጥ የእንግሊዝኛ ፊደላት ከሚከትቡበት ኣንዳንድ ዘዴዎች ጋር የተቀራረበ ነው። በተጨማሪም ቍጥሩ 20090179778(http://www.google.com/patents/US20090179778) የሆነውን የግኝቱን ገለጻ የኣሜሪካ መንግሥት ከኣተመበት ሓምሌ ፱ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ወዲህ የዶክተሩን ጽሑፍ የጠቀሱና የግኝቱን ዘዴ በመጠቆም ሰባት ኣዳዲስ የኣሜሪካ ፓተንቶች ለሌሎች ተሰጥተዋል። ቀደም ብሎ ለዶክተሩ ስለተሰጠው የመጀመሪያው የባለቤትነት መብት እዚህ (http://www.ethiomedia.com/1011issues/first_ethiopic_patent.pdf) ቀርቦ ነበር።
በዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ዕውቅና የተሰጠባቸውን ሁለት ፓተንቶች በመጠቀም ግዕዝኤዲት (GeezEdit) በመባል በታወቀው ፕሮግራም በዊንዶውስና ማክ ኮምፕዩተሮችና ኣይፎን የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እየተጠቀሙ ከኣሉት መካከል ለኤክስፒ ኮምፕዩተር የተሠራው ከዘጠኝ ዓመታት በኋላም ዊንዶውስ 10 ውስጥ እያገለገለ ነው። (http://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%8A%A5%E1%8B%9D-%E1%8D%8A%E1%8B%B0%E1%88%8B%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%88%A5%E1%88%8D%E1%8C%A3%E1%8A%94/a-19199680) የኣልተሟሉና የተሳሳቱ መክተቢያዎችና ፊደላት በሌሎች እየቀረቡ ስለኣሉ ሕብረተሰቡ ከመታለል እንዲጠነቀቅና ሳይንሳዊ ኣስተሳሰብን መጠቀምና መገንዘብ ይጠቅማል።
ዶ/ር ኣበራ ሞላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓማርኛን ያካተተው የግዕዝ ፊደላችን በኮምፕዩተር እንዲከተብ ያደረጉ የግኝት ሊቅም ናቸው። (http://www.ethiomedia.com/1000bits/facts–about-geez.pdf) ከ፴ ዓመታት በላይ የምርምር ውጤቶቻቸውን በማቅረብና ኣዳዲስ ግኝቶቻቸውን በማጠናከር በትጋት እየሠሩ ነው። (http://patents.justia.com/patent/20150212592)
የዶክተሩ ሙያ እንስሳት ሕክምና ሲሆን በመስኩም ትላልቅ ኣስተዋጽዖዎች ከማድረጋቸውም ሌላ ፓተንቶችም ኣሏቸው። የተለያዩ የዶክተሩን ኣስተዋጽዖዎች የተመለከቱ ዓማርኛ ዊኪፔዲያ ላይ ቀርበዋል። (https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB_%E1%88%9E%E1%88%8B) ለተጨማሪ መረጃ ኢሜይሉ Geezedit@aol.com ነው።
ለኣይፎንና ኣትፓድ