የጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት ስኬት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት ስኬት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ መቶ ቀናት ሆናቸው።ጠ/ሚኒስትሩ በመቶ ቀናት በርካታ ጉዳዮችን አከናውነዋል።በዚህም “ስኬታ” ናቸው የሚሉ አስተያየቶች በርካታ ሆነዋል።ዶክተር አብይ ባለፉት ሦስት ወራት ያከናወኗቸውን ጉዳዮች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደሚከተለው አቅርቦታል።

________

 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት፡_

  1. ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው።

መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … ነበር።

ይህንን ነባራዊ እውነታ ከመቀየር አንጻር ባለፉት 100 ቀናት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው።

1.1. ተስፋን የሚያጭሩ ንግግሮች፦ ገና ወደ ስልጣን ከመምጣታቸውም በፊት “ቃል ይገድላል፥ ቃል ያድናል” ይሉ የነበሩት ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ፣ ባለፉት 100 ቀናትም ይህን እምነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

በበዓለ ሲመታቸው ያደረጉት ንግግር ከላይ የነበረውን የጭንቀት መንፈስ ከመግፈፍ አንጻር ከፍተኛ ሚና ተወጥቷል።

በዚህ ንግግራቸው ስለአንድነት፣ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለዴሞክራሲና የሃሳብ ብዝሃነት ያነሷቸው ሃሳቦች እና ባልተለመደ ሁኔታ እናታቸውንና ባለቤታቸውን ለማመስገን የሄዱበት ርቀት ሰዎች ለውጡን ከምር እንዲያዩት ያስቻለ የመጀመሪያው እርምጃ ነበር።

እስካሁንም ድረስ እንደ ጥቅስ የሚነሱ ዓ/ነገሮች (ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያዊ)፣ ለቀጣይ ስራዎቻቸው መነሻ የሆኑ አቅጣጫ አመላካቾች (የኤርትራ ግንኙነት)፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የምር የማስፋት እርምጃዎች፣ … የተንፀባረቁበት ንግግር ነበር።

ከዚህም በኋላ በየክልሉ ባደረጓቸው ንግግሮች የየአካባቢውን ቋንቋ በመቀላቀል፣ የአካባቢውን ባህል በማንጸባረቅ፣ የምር የሚያማቸውን ጉዳይ ከልብ በመስማትና የሚያረካ ምላሽ በመስጠት ሁሉም ተስፋ እንዲያድርበትና ለለውጡ ድጋፉን እንዲሰጥ አድርገዋል።

1.2. ጉብኝቶች፦ ባለፉት ሶስት ዓመታት ችግር ፀንቶባቸው የነበሩ አካባቢዎችን ቅድሚያ በመስጠት በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በመገኘት ንግግር ለማድረግና ህዝቡን ለማወያየት ባለፉት ሶስት ወራት እረፍት የለሽ ጉዞዎችን አድርገዋል።

በዚህም በደረሱበት ሁሉ የአካባቢውን ቋንቋና ባህል በማንጸባረቅ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሪ መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል።

1.3. የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፦ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል።

ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት የፖለቲካ አመራር እስረኞችን መፍታት፣ በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩ የሃገር ውስጥ ድርጅቶችን መሰረዝ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ‘ተፎካካሪ’ እያሉ መጥራትና አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረብ (በቤተመንግስት ተገናኝቶ መወያየት)፣ ለማፈን በርካታ ገንዘብ ይወጣባቸው የነበሩ ሚዲያዎችን መተውና ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረብ፣ ታግተው የነበሩ በርካታ ድረገፆችንና ጦማሮችን ነጻ መልቀቅ፣ …. ይጠቀሳሉ።

እነዚህ ውሳኔዎች ለውጡ የምር መሆኑን በማሳየት መንግስትን በመቃወም ለበርካታ ዘመናት የኖሩ ግለሰቦችና ድርጅቶችም ሳይቀር ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከለውጡ ጎን እንዲቆሙ አድርጓቸዋል።

ይህ የይቅርታ ምህረት አሰጣጥ ሂደቱ ወጥ እንዲሆን የምህረት አዋጅ ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በመንግስት ቤት ውስጥ ያሉ ችግሮችንና ክፍተቶችን በፓርላማ ሳይቀር በግልፅ በማንሳት ‘እኛም አሸባሪ ነበርን’ እስከማለት መድረሳቸውና ይህን ችግር ለመቅረፍም መሰረታዊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸው ተጠቃሽ ክስተት ነው።

ሚዲያዎች በአጠቃላይ (የመንግስት ሚዲያዎችም ጭምር) በነጻነት እንዲዘግቡና በመንግስትም ጭምር ያሉ ክፍተቶችን ያለገደብ እነዲዘግቡ በመደረጉ በተለይ በእስረኞች አያያዝ ላይ የተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ማጋለጣቸው የሚጠቀስ ነው።

ከዴሞክራሲ ምህዳር መስፋት ጋር ተያይዞ ሊጠቀስ የሚችለው ባለፉት ሶስት ወራት በበርካታ አካባቢዎች የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው።

እነዚህ ሰላማዊ ሰልፎች የተለያዩ አርማዎችና ሰንደቅ ዓላማዎች የታዩባቸውና የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉባቸው ናቸው።

ዴሞክራሲ ማለት ትክክል የሆነው ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ ሃሳብም ቢሆን ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ የሚንጸባረቅበተን እድል መፍጠር በመሆኑ፥ እነዚህ መድረኮች መፈጠራቸውና በህዝቡ ልብ ውስጥ ያለው ነገር መንጸባረቁ መልካም ጅምር ነው።

1.4. የደህንነት ተቋማት ሪፎርምና የአመራሮች መቀያየር፦ ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ ብዙ ትችት እና የእምነት ማጣት ስሜት ያስተናግዱ ከነበሩ ተቋማት ዋነኞቹ የደህንነት ተቋማት ናቸው። በእነዚህን ተቋማት ማሻሻያ ማድረግና አስፈላጊ በሆነባቸው ቦታዎች የአመራር ለውጦችን ማድረግም አንዱ የለውጡ አካል ነበር።

የአመራር ለውጡ በደህንነት ተቋማትም ሳይገደብ በሁሉም ተቋማት ላይ በእውቀት፣ ክህሎት እና የአመራር ብቃት ላይ የተመሰረተ ድልድል ተደርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፥ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርን እና ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምን በክብር የመሸኘት ተግባራት ተከናውነዋል። ሌሎች ነባር አመራሮችም በጡረታ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል።

  1. በዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ረገድ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከፍተኛ ልዩነት ከፈጠሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የውጭ ግንኙነት ነው። በዚህም ከኤርትራ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን ‘ሞት አልባ ጦርነት’ ማፍረስ፣ ከዓለም አቀፍ ሃያላን አገራት ይልቅ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ መስጠት፣ ከዚህ በፊት ይህን ያህል የጎላ ግንኙነት ተፈጥሮባቸው ያልነበሩ አገራት ጋር መልካም ቁርኝት መፍጠር እና ከጎረቤቶች ጋር አዳዲስ ጉዳዮችን ያካተተ የስምምነት ማዕቀፎችን መፍጠር ይጠቀሳሉ። ከዚህ አንጻር ዋና ዋናዎቹ ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው።

2.1. ኢትዮ-ኤርትራ፦ ከኤርትራ ጋር የነበረው ‘ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ’ ውጥረት ለመፍታት መልካም ጅምር መፈጠሩ ቀዳሚው ውጤት ነው። በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል ተደንቅሮ የነበረው ‘ጥቁር መጋረጃ’ ተቀዷል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደምም የሰላም ጥሪዋን ለኤርትራ በተደጋጋሚ አስተላልፋ የምታውቅ ቢሆንም፥ በኤርትራ በኩል በግን ‘የኢትዮጵያ ወታደሮች የዓለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት ከወሰነልኝ ቦታ እስካልወጡ ድረስ አልደራደርም’ በማለት ይመልስ ነበር። ባለፉት ሶስት ወራት በተደረጉ ጥረቶች ግን ይህን ቅድመ ሁኔታ በመተው ልዑካኑን ልኮ ወደ ውይይት ገብቷል። ጠ/ሚ/ር ዐብይም ይህን የሰላም ፍላጎት እውቅና ለመስጠት በሚመስል መልኩ ልዑካን ቡድን በመላክ ፈንታ ራሳቸው ወደ አስመራ በመጓዝ የሰላም ምክክር ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ አጉነውታል። በአስመራ የነበረውን የኤርትራውያንን አቀባበል ያያ ማንኛውም አካል ይህን የሰላም ጥረት ወደ ኋላ ለመመለስ ይዳዳዋል ማለት ይከብዳል።

2.2. የጎረቤት አገራት ቀደምትነት፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሶስት ወራት ውስጥ ወደ ሁሉም የጎረቤት አገራት ጉዞ ያደረጉ ሲሆን የደቡብ ሱዳንን ፕረዝዳንትና ተቃዋሚም በአዲስ አበባ አግኝተው አወያይተዋል። በዚህም ቅድሚያ የሚሰጡት ለጎረቤት አገራት እንደሆነ አሳይተዋል። በፖለቲካ ሳይንስ እንደሚባለው፥ “ማንኛውም አገር ወዳጅ አገር የመምረጥ መብት አለው፤ ጎረቤት አገር ግን አይመርጥም”። ጎረቤት አገር በብዙ ረገድ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው። ጠ/ሚሩም ይህን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ለከባቢያዊ ጉዳዮች ቅድሚያውን ሰጥተዋል።

2.3. በአዳዲስ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መድረስ፦ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ከጎረቤት አገራት ጋር በነበረው ግንኙነት በሰጥቶ መቀበል መርህ የተመሰረተ የመጠቃቀም አካሄድ እንዲኖር ቢሰራም ባለፉት 100 ቀናት የተደረጉት ድርድሮች ግን ከዚህም ላቅ ያሉ ነበሩ።

ከጂቡቲ ጋር በተደረገው ውይይት የወደብ ድርሻ የመግዛትና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ውጤታማ ድርጅቶች መሃል የአየር መንገድና የኤሌክትሪክሲቲ ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥብ ሃሳብ ቀርቦ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ይህም ኢትዮጵያ ውድ ዋጋ ከምታወጣለት የወደብ አገለግሎት ተጠቃሚ እንድትሆን በማድረግ የተረጋጋ የወደብ አገልግሎት ዋጋ እንዲኖር ያደጋል። ቀስ በቀስም ይህ ድርሻ እያደገ ከሄደ በተለይ ከደህንነት አንጻር የሚኖሩ ውስንነቶችን ሊቀርፍ ይችላል።

2.4. በቀይባህር ጉዳይ ላይ ተይዞ የነበረው ቸልተኛ አቋም መለወጥ፦ በቀይ ባህርና ኤደን ባህረሰላጤ የተለያዩ ዓላማዎችን ያነገቡ በርካታ ሃይሎች ማንዣበብ ከጀመሩ ቆየት ብለዋል። በተለይ የየመን የእርስ በርስን ግጭት ተከትሎ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስትና አማፂያንን በመደገፍ በርካታ የአረቡ ዓለም መንግስታትና ኢራን በሁለት ጎራ ተከፍለዋል። ኢራን፣ ኳታር፣ ቱርክ እና ሱዳን በአንድ በኩል፤ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ባህሬን እና ግብፅ በሌላ በኩል ሆነው የየመንን ምድር የጦር አውድማ አድርገዋታል።

ለዚህ ስምሪትም በተለይ ኤርትራ ላይ የተለያዩ የጦር ሰፈሮችንና ቤዞችን አቋቁመዋል። ግብፅም በዚህ አስታካ ኤርትራ ላይ የጦር ቤዝ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምራ ነበር። በዚህ የአገራት አሰላላፍ ውስጥ ኢትዮጵያ የነበራት ሚና ከሁለት አንዱን በመምረጥ ላይ ያልተመሰረተ ነበር። ይህ መሆኑ ከሁለቱም ጥቅም ለማግኘት የማስቻል እድል ቢኖረውም ጉዳቱ ግን ከፍ ያለ ነበር።

ይህን እውነታ ከመቀየር አንጻር ባለፉት ሶስት ወራት በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል። በዚህም በተለይ በሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጉብኝት በብዙ ረገድ ፈር ቀዳጆች ሲሆኑ፤ ከግብፅ እና ኤርትራ ጋር ቀጥለው ለተደረጉት ውይይቶችም አስቻይ ሁኔታን የፈጠሩ ነበሩ። (የኤርትራው ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ የመጣው በዱባይ አየር መንገድ ልዩ በረራ እንደሆነ ልብ ይሏል!)

በቀይባህር እና በኤደን ባህረሰላጤ የሚከናወኑ ጉዳዮች በከፍተኛ ሁኔታ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩባቸው አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።

በመርከቦች ጉዞ መታወክ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ከሚፈጠረው የኢኮኖሚ ጫና በተጨማሪ የአገሪቱ የኢንተርኔት መግቢያ በር በቀጥታ ልንከላከለው በማንችለው መልኩ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኝ በመሆኑ የደህንነት ፋይዳውም የጎላ ነው።

ከዚህም ባሻገር ግብፅ እንዳቀደችው ተሳክቶላት ቢሆን ኖሮ ምፅዋ ወይም አሰብ ላይ የጦር ሰፈር አቋቋመች ማለት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚኖረው አንድምታ ከፍተኛ ነበር። እንዲህ አይነት ቀጣይ ስጋቶችን ከመቀነስ አንጻር ባለፉት 100 ቀናት የተደረጉት ዋና ዋና እርምጃዎች፥ ከሁሉም ጎረቤት አገራት ጋር በወደብ ኢንቨስትመንት መተሳሰር እና የባህር ሃይልም የማቋቋም ፍላጎት መንጸባረቅ የሚጠቀሱ ናቸው።

  1. በኢኮኖሚ ረገድ፦ የሃገራችን <span lang=”AMH” style=”font-family

LEAVE A REPLY