/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ ነው ተባለ። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ መሆኑን የኤርትራ ሚዲያ ተቋማት ዘግበዋል። ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ የእሁዱ የኢትዮጵያ ጉብኝት እ.ኤ.አ ከ1998 ወዲህ የመጀመራቸው እንደሚሆንም ተጠቅሷል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጉብኝታቸው ወቅት በግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ ከተለያየ ማህበረሰብ ለተውጣቱ ኢትዮጵያዊያን ንግግር እንደሚያደርጉም ታውቋል።
በአዲስ አበባ ስቴድየም አካባቢ የሚገኘው የቀድሞው የኤርትራ ኢምባሲም ፈጣን ጥገና እየተደረገለት ሲሆን በአጭር ጊዜ ኤምሳሲው ስራ እንደሚጀምር እየተገለጸ ነው።
ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ክብር በብሔራዊ ቤተ_መንግስት በሚደረግ የእራት ግብዣ ላይ ለዓመታት ስለ ኤርትራና ፍቅር ሲያቀነቅን የኖረው ቴዲ አፍሮና ሀጫሉ ሁንዴሳ እንደሚያዜሙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።
የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ወደ አስመራ በማቅናት በርካታ መልካም ነገሮችን አከናውነው መመለሳቸው ይታወሳል።