በሞያሌ ዳግም ውጥረት ነግሷል፤ የሰዎች ህይወትም እየጠፋ ነው

በሞያሌ ዳግም ውጥረት ነግሷል፤ የሰዎች ህይወትም እየጠፋ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በሞያሌ ወረዳ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።በርካታ ሰዎችም መሞታቸውን በምስል የተደገፉ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።ከአንድ ሳምንት በፊት  በጋሪና በቦረና ጎሳዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት አሁንም እየተባባሰ ይገኛል።

“Somali Region Alliance for Justice” የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ትናንት ባወጣው መግለጫ የሟቾች ቁጥር 50 እንደሚደርስና ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ዜጎችም በጥይት መቁሰላቸውን ገልጿል።ለጉዳዩ የፌዴራል መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡትና መፍትሔ እንዲያበጁ ተማፅኗል።

 ዛሬም ግጭቱ ተባበስሶ የዋለ ሲሆን በምዕራብ ሐረርጌ ዞን መኢሶ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ በተከፈተ ጥቃት ሶስት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሰባት ንፁሃን ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ደረሰ በተባለው ጥቃት የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል መሳተፉን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና የመኢሶ ወረዳ ነዋሪዎች ከሶማሌ ልዩ ሀይል የተቃጣባቸውን ጥቃት መመከት በመጀመራቸው አካባቢው የጦር አውድማ ሆኖ መዋሉም ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ከሰዓት በሗላ ወደ ስፍራው ማቅናቱም ተጠቁሟል።በሞያሌ ከተማም በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መስፈራቸውን ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY