/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢንጂነር ታከለ ኡማ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው ዛሬ ተሹመዋል። ኢንጂነር ታከለ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በከንቲባ ማዕረግ ምክትል ከንቲባ ሆነ የአቶ የድሪባ ኩማን ወንበር ተረክበዋል።
ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ መሾማቸውን የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ቴሌቪዥን ዘግቧል
አቶ ታከለ በዶክተር መረራ ጉዲና ይመራ በነበረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) አባል የነበሩ ሲሆን በወቅቱ በፓርቲው ውስጥ በነበረ አለመግባባት ለሁለት ሲከፈል የእሳቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። አቶ ታከለ ኡማ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ ታሪክ 31ኛው ከንቲባ መሆናቸው ታውቋል።
ተሰናባቹ ድሪባ ኩማ አዲስ አበባን ለአምስት ዓመታት በከንቲባነት የመሩ ሲሆን በቅርቡ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።