ኤርትራ “አዲ አበይቶ” የተባለውን ወህኒ ቤት መዝጋቷ ተነገረ እስረኞች እንዲፈቱ እየተጠየቀ ነው

ኤርትራ “አዲ አበይቶ” የተባለውን ወህኒ ቤት መዝጋቷ ተነገረ እስረኞች እንዲፈቱ እየተጠየቀ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ በርካታ እስረኞችን የያዘው አዲ አበይቶ የተሰኘውን ማረሚያ ቤት መዝጋታቸው “ራዲዮ ኢረና” የተባለ ሚዲያ ዘገበ።

እንደ ዘገባው ከሆነ በእስር ቤቱ ውስጥ የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አንሳተፍም ያሉ በርካታ ኤርትራውያን የታሰሩበት መሆኑ ታውቋል። በዛሬው እለት ወህኒ ቤቱ የተዘጋና እስረኞቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል።

እንደ ራዲዮ ኢረና ዘገባ አራት መቶ(400) የአንጀሊካን እምነት ተከታዮች ከእስር ቤት ተለቀዋል። ኤርትራ እ.ኤ.አ. 2002 በሀገሪቱ ውስጥ የኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ሉተራን እምነትና የሱኒ እስልምና ውጭ በህግ መከልከሏ የሚታወስ ነው።

አቶ ኢሳያስ ከአዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ የፖለቲካ አመለካከታቸው  የተለየ ነው በሚል ያሰራቸውን ጓደኞቹውንና ጋዜጠኞችንና ጨምሮ በተለያዩ ማሰቃያ ቦታዎች ያጎሯቸውን ንጹሀን ዜጎች ይፈታሉ ተብሎ ቢጠበቅም አስካሁን ይህ ነው የሚባል እርምጃ ሲወስዱ አልተስተዋለም።

ሂዩማን ራይትስ ዎች የኤርትራ መንግስት የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር የሚጠይቅ ጠንካራ መግለጫ ዛሬ አውጥቶ ነበር።

LEAVE A REPLY