የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ እያነጋገረ ነው

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ እያነጋገረ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማለት ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን የዳያስፖራውን እንቅስቃሴ ለማቀናጀት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ” በሚል የሂሳብ አካውንት ተክፎቶ ስራ መጀመሩን የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት የትረስት ፈንድን አስፈላጊነት ባቀረቡት ሃሳብ መነሻነት የተከፈተው አካውንት ጊዜውን ያልጠበቀና የሩጫ ሂደቱ ብዙዎች እንዲያፈገፍጉ የሚያደርግ ነው የሚሉ አስተያየቶች እያስተናገደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሃሳብ እጅግ ጠቃሚና ለሀገር ግንባታ ሂደቱ አስፈላጊ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች በይድረስ ይድረስ መሰረቱ ለስኬታማነቱ ደንቃራ እንዳይሆን እንደሚሰጉ ገልፀዋል። ዶ/ር አብይ ፈጣን የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ በአጭር ጊዜ ያስመዘገቡት እመርታ ያስደሰታቸው መሆኑን የገለጹት እኒህ የፖለቲካ ተንታኝ የገንዘብ ስብሰባው ሂደት ለሀገሪቱ ዘላቂ መረጋጋት መፍተሄ የሆነው የነጻ ተቋማትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተቱ ውይይቶችና መግባባቶች ሳይከናውኑ የገንዘብ ስብሰባ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ከማለታቸውም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለምን አገልግሎት እንደሚውልና ዳያስፖራውን ያካተቱ ውይይቶችና ወካይ ቦርድ ሲያቋቋም በዘፈቀደ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ነገ ድረገጽ አስተያየታቸውን በመስጠት የሚታወቁት እኒህ ተነተኝ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው እንዳሉት ለሴቶች፣ በወሊድ ለሚሰቃዩ እናቶች ወይንም ለእድሜ ባለፀጎችም ሆነ ለሌሎች ተግባራት የሚውል ከሆነም በገለጽ መናገር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ(Ethiopian Diaspora Trust Fund) የባንክ አካውንትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ_ 1000255726725 መሆኑ ተገልጿል።

የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት በየጊዜው በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን የሚሰበሰበው ገንዘብ በይፋ  ላልተነገረው ለታለመለት አላማ እንደሚውልም ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY