የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስ ቡክ ገፃቸው እንደገለጹት ከቡኖ በደሌ ዞን ከመንግስት ባልስልጣናትና የከተለያየ የማህበረሰብ አካላት የተውጣጡ አካላት ከተፈናቃዮች ጋር ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
አቶ ንጉሱ በፌስ ገፃቸው ላይ የሚከተለውን መልዕክት አስፍረዋል።
———
ቀደም ሲል ከኦሮሚያ ቡኖ በደሌ ዞን ተፈናቅለው በባህር ዳር እና ሰሜን ወሎ የሚገኙ ወገኖችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እና ለማቋቋም በቂ ዝግጅት በመደረጉ ተፈናቃዮችን ለመመለስ እና በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክቡር ዶክተር ግርማ አመንቴ (በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ )፣ ክቡር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ አቶ ለጥይበሉ ሞቱማ እና አባ ገዳ ተሾመ በቀለ የተካተቱበት የልዑካን ቡድን ባህር ዳር ተገኝቶ ውይይት አድርጏል::
በመድረኩ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኩል የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተገኙ ሲሆን መልዐከ ብርሀን ፍሰሀ የሺሀሳብ ተገኝተዋል::
ከኦሮሚያ ክልል የመጡት የልዑካን ቡድን መሪ ክቡር ዶክተር ግርማ አመንቴ የክልሉ መንግስት ይህንን ሁኔታ የሚከታተል አንድ የአመራር ቡድን አደራጅቶ እ ናንትን ለመቀበል ዝግጁ ነው ብለዋል:: አቶ ለጥይበሉ ሞቱማ በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብ እና አመራሩ እናንተን ወደ ቤታችሁ እንድትመለሱ ዝግጅት አድርጏል፤ በየአካባቢው ከህዝብ ጋር ውይይት ተደርጎ ህዝቡ ወገኖቻችንን አምጡ ብሎ ነው የላከን ሲሉ አስረድተውል::
እስክትቋቋሙ ድረስ እንደግፋችኇለን፤ የፀጥታውን ሁኔታም ከእናንተው ጋር ሆነን አስተማማኝ ለማድረግ እንሰራለን፤ በኛ እና በህዝባችን ላይ እምነት ጣሉብን በማለት ተፈናቃዮችን ጠይቀዋል::
በመጨርሻም ተፈናቃዮች ነገሮች ከተስተካከሉ እና አስተማማኝ ሁኔታ ከተፈጠረ እንመለሳለን ግን ይህንን ማረጋገጥ ይገባናል በማለት እያንዳንዳቸው እንዲወስኑ ስምምነት ላይ ደርሰናል::