ልጓም ይበጅለት ትንሺ ተለጠጠ /ሰመረ አለሙ/

ልጓም ይበጅለት ትንሺ ተለጠጠ /ሰመረ አለሙ/

ያዋከቡት ነገር ምራፍ አያገኝም ፍቅሬ ቅሬ በዛ እኔ አላማረኝም

ነበር ያለዉ እዉቁ የኢትዮጵያ ልጂ ጥላሁን ገሰሰ ለዚህ ቀን ሳይደረስ አለፈ አንጀቱ እንደተቃጠለ በሻቢያና ህወአት።

ህወአት የተባለ የጭራቅ ስብስብ በመለስ ዘራዊ;አረጋዊ በረሄ፤ስብሀት ነጋ፤አባይ ጸሀዬ፤ስዩም መስፍን፤ ሰየ አብረሀ፤ ብስራት አማረ፤ ግደይ ዘራጽዮን …… አማካይነት አገችንና ህዝባችንን ቁም ስቅል ሲያሳይ ከርሞ የራሱ ትብትብና ሰይጣናዊ ሰራዉ ተደምረዉ ራሱኑ ጠልፈዉ ጥለዉት በማጣጣር ላይ ይገኛልመቼም ክፉ ሰዉም ሆነ ድርጅት ሲኖርም ሲጠፋም ለነዋሪዉ ጠንቅ በመሆኑ የዶ/ር አብይን ህይወት ለመቅጠፍ ያደረገዉን አስነዋሪ ተግባር ተመልክተበእጂጉ አዝነናል

በስልሳዎቹ የወከባ ዘመን ይሄ መላ ቅጡ የጠፋ ጉዞ ልጓምይበጅለት ነገሮችን በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አዛምደን እንመልከት ብሎ የሰከነ ምሁር ሲያመላክት የነ ቼ ጉቬራ ልጆች ወዲያዉ የሰብጥር ተኩስ ከፍተዉ በእምነቱ በህልዉናዉ ላይ ከማነጣጠር አልፈዉ በጥይት መትተዉይጥሉት እንደነበረ ከታሪክና ከጥይት የተረፉት ምሁራንማስረጃተዉልና ስንቱ ለአለም የሚተርፍ ምሁር እንደ አዉሬ በገዛ ሀገሩና ወገኑ ታድኖ ጠፋ ቤተሱም ተበተነ እዉቀቱም መና ሁኖ ቀረ ሀገርም ያወጣችበትን ሳትመልስ ከሰረች እነዚህ ተማሪዎች ሻቢያ ህወአትሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ታግዘዉ ደርግን ሀ ሁ አስቆጥረዉ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረጉትን ትዉልዶች ካስደመሰሱ በሗላ በተራቸዉ በደርግ ተበልተዉ ደርግ በትረ መንግሰቱን ከተቆጣጠረ በሗላ ደረሰዉን ጥፋት ዛሬ በህይወት የቆየዜጋ በሚገባ ያዉቀዋል ብዬ እገምታለሁ። በወቅቱ ሰዉ ከቤቱ ወጥቶ ለመግባቱ ዋስትና አልነበረም ። በዚህ አንጀቱ የበገነዉ ህዝባችን ደርግን ባይተዋር አድርጎ በመመልከቱና በመጥላቱ እፍኝ ለማይሞሉ ለትግሬና ለሻቢያ ፋሺስቶች በሩን ከፍቶላቸዉ ወደ መናገሻያለ ችግር ገቡ።

ህዝብ የጠላዉንና የተዋጋዉን የደርግ መንግስት በጀግንነት ጣልን ተራራን አንቀጠቀጥን ብለዉ እነ አረጋዊ በርሄና ደቀመዝሙሮቻቸዉ ሰበኩ ተዘባነኑ ህዝብን ናቁየኢትዮጵያንም እሜ ወደ 100 ዝቅ አደረጉት ይህንን ጥጋብ የተመለከተ የኢትዮጵያ አምላክ ሻቢያን አስነስቶ ምድር ቀዉጢ ስትሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የዛሬን ቅበረን ካሁን በሗላ አናስቀይምህም ብለዉ ቢማጸኑ ህዝርህሩህ በመሆኑ ከሻቢያ መንጋ አዳናቸዉ ታደጋቸዉ ወጣቱ ተንኮላቸዉን ባለማወቁ እነሱን ለማዳን ለመሞት ተሽቀዳደመ። ታዲያ እነዚህ የእፉኝ ልጆች የኢትዮጵያ ሰራዊት የሻቢያን ወራሪ እያሳደደ ከቀጣና ከባረረ በሗላ ወደ አሰብ በመገስገስ እያለ ጦሩ እንዲመለስ አደረጉት ትንፋሽም ሲገዙ ወደ ንኮላዉ ተመለሱ። የሚገርመዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት በተቆጣጠረዉ ቦታ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ሳይሆን የትግራይ ክልል ጨርቅ አዉለበለቡ በዚህ የተገረሙት የዉጭ ሀገር ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ትዝብታቸዉን በየአምዳቸዉ አሰፈሩ። ታዲያ ይህን ክህደታቸዉን የተመለከተ የኢትዮጵያ ሀዘብ በተራዉ መለስ ዜናዊ/ስዩም መስፍንና ህወአት ለሻቢያ የሰቸዉን አካባቢዎች አብይ ተግባራዊ ሊያደርገዉ ሲሞክር ቢጮሁ ዳር ድምበር ተደፈረ እዛዉ ጣጣችሁን ቻሉት በማለት በተራዉ ያላግጥባቸው ጀመር  አይን ላጠፋ አይን ሁኖበት እነሱም የሚያደርጉት ጠፍቷቸዉ መቀሌ ተሰብስበዉ ይላቀሳሉ

ታዲያ ያለንበት ሁኔታ እንዲህ ሁኖ እያለ ዶ/ር አብይ በየግግሩ ይቅር ባይነትን አጉልቶ ስጮኸዉ ይሰማል ይቅርታ ጥሩ ነዉ ነገር ግን  ይቅርታ የሚደረገዉ በስህተት ላጠፋ፤ ላላመዛዘነ ግብታዊነት የማይፈለግ ነገር ላደረገ  ባስተሳሰብ ሚዛን ለተጎዳ ዜጋ ሁኖ ሳለ በኢንስቲቱሺንናበከፍተኛ ጥናት ሆነ ብለዉ በደል የፈጸሙትን ይቅርታ ከለፊታችሁ ተዘጋጅቷል አይዟችሁ የሚል አካሄድ ትክክል አይመስልም ወደፊትም ወንጀልን ያደፋፍራል

የሚገመዉ በተለያየ ደረጃ ዜጋን የቀጠፉ፤ሀብት የዘረፉ፤በሀገርና በህዝብ ያላገጡ እስከ ክብራቸዉ አንዴ በጡረታ አንዴ በአማካሪነት አንዴ በአምባሳደርነት ጠ/ሚኒስተሩ አካባቢ ዉርዉር ሲሉ ሰናይ ስጋታችን ጨምእንደዉም ይህንን ያስተዋለዉ በለጠ ባሹ በአዋሳዉ ስብሰባ ጨዋ አነጋገር አካባቢህ በሌባና በነብሰ በላ ተከቧል በህዝብ ፊት ነዉ የተናገሩት ለዚህም ዋስትና ትሰጡኛላችሁ በማለት የሰጠዉ አስተያየት ሳይዉል ሳያድር በ ጠ/ሚኒስተሩ ላይ የተደረገዉ የግድያ ሙከራ ለትክክለኝነቱ ማረጋገጫ ሁኗል። ታዲያ በለጠ ባሹ የተናገረዉ ከግምት ባለመወሰዱ ሺፈራዉ ሺጉጤ ከህወአት አለቆቹ ቀጥተኛ ትእዛዝ በመቀበል በገዛ ወገኖቹ ላይ ዘመ ያየነዉ እልቂት ሁኗል ። አሁንም በዶ/ር አብይ ይቅር ባይነት ፎርሙላ ከክክልሉ እንዲሰናበት ሲደርግ ለሰራዉ ወንጀልና ጥፋት ወደ ቃልቲ ሳይሆን በሙሉ አምባሳደርነት ወደ አንድ ትልቅ ሀገር እንደ ተላከ ከተባራሪ ወሬ ይሰማል

ከ1000 ወጣት በላይ ኢቻ በአል ላይ የተቀጠፈዉ ወጣት ፍትህ ይፈልጋል፤ ሰብአዊ ባልሆነ መልኩ ብልታቸዉ ላይ ኮዳ እየተንጠለጠለ የተኮላሹት  ጥፍራቸዉየተነቀ፤ የተገረፉና አስነዋሪ ስራ የተሰራባቸዉ ዜጎች ፍትህን ይጠብቃሉ። የሺብሬ ደሳለኝ እናትና ልጇን ገድለዉ ሬሳዉ ላይ እንድትቀመጥ ያደረጓት እናት ፍትህን ከኢትዮጵያ ህዝብ ትጠብቃለች። የሓብታሙ አያሌዉ፤ እስክንድር ነጋ፤አንዱ አለም አራጌ  ቁስል ዛሬም አልሻረም። እንደ ዶር አብይ እናት ካሉብት አገር ወጥተዉ አገራችን ብለው በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ሰፍረዉ ለአካባቢዉ እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ዜጎች በነ ጁዋር መሀ ህዝቅኤል ጋቢሳ ጸጋዬ አራርሶ፤ በህወአትና መሰል ድርጅቶች ቅስቀሳ በደረሰባቸዉ በደል ፍትህን ይጠብቃሉ።

ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ ዜጎች ተጋዙ ተገደሉ ቤት ንብረታቸዉ ጋየ በሀገራቸዉ ተዳጂ ሆኑ ይህንን ማንሳት ዛሬ ሊያሸማቅቅ አይገባም ፍትህ ያስፈልገዋል ኢትዮጵያ መልሳ ስትቋቋም መርረማሪ ኮሚሺን ተቋቁሞ ሪፖርቱ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ይደረጋል እዚህ ላይ ሰብአዊነት ላይ የደረሰዉን ወንጀሉን ማለታችን እንጂ የኢኮኖሚ ወንጀሉ በእጂጉ ዘግናኝ ነዉ በጠራራ ጸሀይ የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት ወስደዉ ትልቁ ኢንቨስተር ወአት ነው ብለው በግልጽ ነግረውና የተበደሩት ገንዘብ ካለመመለሳቸዉም በላይ ታክስ የሚባልም አያዉቃቸዉ በኢትዮጵያ የቀን ጅቦቹ የልብ ልብ በማታቸዉ አየር መንገዱን፤ ቴሌኮሚኒኬሽኑን አገሪቱ ያላትን አንጡራ ሀብት ቶሎ ሽጡል እያ በገሀድ መጠይቅ ዘዋል።  የሌቦች አለቃ አባይ ጸሀዬ በአሶሳ በረከት ሰሞን በአማራ እነ አርከበ አዲሳ አበባ እ አብረሀ ደስታ/ገብሩ አስራ ከወደ መቀሌ አገር ብተና ስራቸዉን ተያይዘዉታል ወንጀለኞችን እየመለመሉ ወደ መሀል አገር ይልካሉ።

ዶ/ር አብይ በባህር ዳር ጉባኤዉ አንዱ ወጣት እርሶ በሚያስተዳድሩት ኦሮምያ አማራዉ በጅምላ ተገድሏል ተሳዷል 5 ሚሊዮን ከቁጥር ጎድሏል በተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ሴራ በአመንካኝ መድሀኒቶች ቁጥሩ ቀንሷል ብሎ ቢጠይቅ ዶ/ር አብይ የሰጠዉ ምላሽ አጥጋቢ አልነበረም ለምን የአማራዉ ሰቆቃ ዘልቆ ስብእናዉ ላይ እንዳልደረስ ግልጽ አይደለም። ይህ ሁኔታ ዛሬ ይዳፈን እንጂ የዚህ ግፍ ተዋንያን ለፍርድ ሳይቀርቡ ሀገር ሰላም ያገኛል ማለት ዘበት ነዉ። እዚህ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ልጅ ለማ መገርሳ በነጁዋር ምህርት ተገፋፍተዉ በትሬ ካድሬዎች ድጋፍ አማራዉ ላይ በደል ያደረሱትን ጥቂት ካድሬዎች ማባረሩ በሰብአዊነት ስም ክብር ሊቸረዉ ይገባል። በእርግጥ እነዚህ የራሳቸዉ አስተሳሰብ የሌላቸዉ ሰዉ የሚያስብላቸዉ የሚሰሩትን ስራ በርቀት (በሪሞት ኮንትሮል) እነ ጁዋር መሀመድ፤ህዝቅኤል ጋቢሳ፤ጸጋዬ አራርሳ የሚቆጣጠሯቸዉ ለሰከነ ኦሮሚያ ጥቅም ይሰጣሉ ብለንም ስብም ።

ሳለፍነዉ የመከራ ጊዜ አንጻር ጊዜያዊ እፎስላገኝን ዶር አብይ አሊንና ጀግናዉ ለማ መገርሳን ዘር ጎሳ ሳንለይ የመጡበትንና የሚያገለግሉትንና የቀደመዉን ታሪካቸዉን ከግምት ሳንወስድ ተቀብለናቸዋል። ቀደም ባለዉ ጊዜ የዶ/ር ብርሀኑን ድርጅትና የመሪነት ችሎታ ከግምት የሚከት አንድ ጽሁፍ ወደ ድር ገጹ ተልኮ ነበር(www.ethiosun.com/archives/225563)። በንጽጽር ዶ/ር አብይንም የምንለካዉ በዚሁ መስፈርት ይሆናል። ድፍረቱን አገር ወዳድነቱን ለሁኔታዎች ፈጣን መልስ መስጠቱን ለሃገር ዳር ድምበርና ለባንድራዉ ሟች መሆኑን ተቀዳሚ ሁኖ ዝርዝሩ የዜጎችን አንድነትና እኩልነ ማስጠበቅ ሁኖ ለዜጎች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍትህን ማስፈን የዚሁ ተግባር አካል ይሆና

ዶር አብይ ወታደር፤የደህንነት ሰዉ ሁ ለህዝብ ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት በመጣበት ጊዜ ያስተዋልነዉ ሁኔታ ይህንን ልምዱን ጥያቄ ዉስጥ የሚከት ሁኗል። ጌታቸዉ አሰፋ ከጎኑ አርከበ እቁባይም እንዲሁ በቅርብ ሁኔታዉን ይቆጣጠሩትነበር። አርከበ እቁባይ ናቅፋ የኢትዮጵያ ወታደር በቁጥጥር ሰር ሊያገባት ትንሺ ሲቀረዉ 5000 የትግሬ ወጣቶችን ይዞ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ አሰቃቂ ወንጀል የፈጸመ በመሀል ከተማችን ሊገኝ የማይገባዉ ወንጀለኛ መሆኑን ለዚህ ጽሁፍ አንባቢዎች መግለጽ ያስፈልጋል በክፉ ስራዉም ተኩራርቶ እንዲኖር እድል ሊሰጠዉ አይገባምለነገሩ ሁሉም የህወአት አባል የጦር ወንጀለኛነቱ እንዳይረሳ ማሳሳሰብ አስፈላጊም ይሆናል

የደህንነትመከላከያ/የፍትህ/ወህኒ ቤት /መገናኛ/የፋይናንስ ተቋማት  ደ/ር አብይ ስልጣን በያበት ምሽት መዋቅሩተለዉጦ አስተማማኝና ለቦታዉ ብቁ የሆኑ ዜጎች ሊይዙት በተገባ ነበር። የህወአትን ወንጀል የሚያሳይ ስፍር ቁጥር የሌለዉ ማስረጃና ማህደር በዶክተር አብይ እጂ ይገኛልእነዚህን የጦርና የኢኮኖሚ ወንጀለኞችን ወደ ወህኒ ጨምሮ የህግ ዉጤቱን መከታተል  በሰለጠኑ የምእራብ አገሮችም የሚሰራበት በመሆኑ ፍርሀትና ጥርጣሬ አይገባም ነበርዶ/ር አብይ በህዝብ ድጋፍ ቢተርም አልሞም ብሎ የሚያስብግብዝ ነዉ እላለሁ። በወቅቱ የታዩት የደህንነት ጠባቂዎች ቅልጥፍናቸዉ ተመሳሳይነቱ ለንደን ኦሎምፒላይ በተደረገዉ የዋና ዉድድኢትዮጵያን የወከለዉን ዋናተኛሮቤል ኪሮስ ሐብቴን ነገር ያስታዉሰናል www.slate.com/blogs/five_ring_circus/2016/08/11/ethiopian_swimmer

ኢትዮጵያን በእንግሊዝ ኦሎምፒክ እንድትሳተፍ  በህወአት ተመርጦ ለመጀመሪያ ጊዜ የተላከዉ አሳ ዋናተኛ ሮቤል ተወዳዳሪ ዋናተኞቹ ዉድድሩን ጨርሰዉ ሲለብሱ ባለመድረሱ ትንፋሺ አጥሮት ሊሰምጥ ይችላል ብለዉ አዘጋጆቹ በመስጋት ነብስ አድን ጠላቂዎች ዳርና ዳር አቁመዉ ይጠብቁት ነበር በሪኮርድ ዉድድሩን እንደ ጨረሰ ሁሉ ከዉሃ ሳይወጣ ጋዜጠኞች ለጠየቁት ጥያቄ አቤል የመሰለዉን በታላቅ ኩራት መልሷል ያለማወቅ ደጉባለስልጣኑ ትግሬ አባቱ ለዉርደት ዳረገዉ ያባት ክፉ ስራ ለልጂ ይተርፋል ማለት ይህ ነዉ አቤል ያለጥፋቱ አለምተሳለቀበት እሱም አቅሜ አይፈቅድም ማለት ሲገባዉ እራሱን ለማይረባ ጥቅም ሲል ለዉርደት ዳረገኢትዮጵያ በተራ ዱርዬዎች መመራቷን ያሳየ ኦሎምፒክ ነበር ባጭሩየዶር አብይ ጠባቂዎችም ቅልጥፍናቸዉ እንደ አቤል ነበርበዚህ ትልቅ በአል የኢትዮጵያ (የትግሬ) ባንድራም የተዉለበለዉ በአቤል ኪሮስ ነበር ። በመሰረቱ የአንድን ሃገር ብሄራዊ ባንድራ በኦሎምፒክ የሚያዉለበልበዉ ለሀገሩ በስፖርት ልዩ አገልግሎት ያበረከተ ባይሰለፍም ለዚህ ክብር የበቃ ብቁ ሰፖርተኛ መሆን ነበረበት ያ ሳይሆን ቀረ አቤል ትግሬ በመሆኑ ብቻ ሳንወክለው በግድ በዚህ ትልቅ በአል ላይ ለዉርደት ወከለን የትሬ ፋሺስቶች መሳቂያ አደረን።

ጾረና/ዘላምበሳ/ባድሜ አሰብን ጨምሮ ወደ ኤርትራ ሂዷል ( ወንድወሰን ተክሉ፤አቻምየለህ ታምሩ ሳተናዉ ድረገጽ) በእርግጥ ትግሬዎች በወያኔ አስተዳደር የችግራችን ተካፋይ አልሆኑም ነጻ ካወጣናቸዉ በሗላም መለስ ዜናዊ የሰጣቸዉን እራፊ ጨርቅ በወንድሞቻችን አስከሬን ላይ ባልወደቁበት ድል በነዚህ ከተሞች አዉለብለዉበታል። በዚህ ልባችን ደምቷል ነገር ግን ኢትዮጵያን ስናስብ ዳር ድምበሯ ከአባቶቻችን የተላለፈዉ ይሆናልከ1000 አመት በሗላ በትግራይ ዉስጥ ብቻ ለመኖሩ ዋስትና አይኖርም የአለም ተለዋዋጭ ሁኔታ፤ደህንነት ድህነት፤ተፈጠሯዊ ክስተት ከግምት ሲገባ ሰለ ነገዉ በአንድ ቦታ መቆየት በረጅሙ ለመተንበይ አስቸጋሪ ይሆናልኢትዮጵያ ግንለዘላለም ለመኖሯ ጥርጥር አይኖር። ከዚህ አንጻር ሲታይ አሁን የተያዘዉ የድበር ድርድር እንደዚህ በይድረስ ይድረስ ባይሆን መልካም ነበር። በእርግጥ ዛሬ የሚንጨጩት ትግሬዎች የዛሬ ተቃዉሟቸዉን ቀደም ብለዉ በመለሰ ዘራዊ ዘመን ጀምረዉት ቢሆን ከጎናቸዉ እንቆም ነበርእነሱ ግን ከተጨባጭ እዉነታ ይልቅ ድረጅታቸዉን አመኑ እኛንም ባይተዋር አደረጉን እዚህ ላይ ትግሬዎች መሬቱን ባይፈልጉትም ወይም ደግሞ ለትግራይ ትግርኛ ምስረታ ይበጀናል ብለዉ ቢያቆዩትም   ከኢትዮጵያ ሉአላዊነት አንጻር  በሃሳብ ደረጃ እንኳን ይህንን የሰሞኑን ዉሳኔ ለየት ባለ መልኩ እንዲታይ መንግሰ ላይ ጫና ማድረግ በተገባን ነበር ምክንያቱም የኢትዮጵየ ሉኣላዊ ግዛት ነዉና ለጊዜው

ኤርትራን በተመለከተ ሐ/ማርያም ደሳለኝ ተንበርክኬ ጉልበት እስማለሁ ሲል ነበር በል ተብሎ ይሆን የራሱ ምልከታ በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም በእርግጥ ሐ/ማርያም የወያኔዎችን ፊት እያየ ፊታቸዉን እየተረጎመ የሚናገር ለይሰሙላ የተቀመ መሪ ነበር። ዶ/ር አብይ ላይ ሲደገም ግን ቅር ይላል። ጎበዝ ኢትዮጵያ ተልቅ ሀገር ነች በዘመኗ የካበተ ታላቅ ታሪክ ያላት አገር ነች አንድ የኢትዮጵያ መሪ ለትላንቷ ጠ/ግዛታችን እንዲህ መነጠፍ ባላስፈለገው ነበርኤርትራኖች ካላቸዉ ችግር በላይ ኢትዮጵያ በችግር አልወደቀችም። አብረናቸዉ ነዉ የምንኖረዉ ማን ምን እንደሚያስብ ጠንቀቅን እናዉቃለን ትግርኛ የማይችሉ አሁንም ኢትዮጵያ የሚኖሩና ተቀማጭነታቸዉ ኢትዮጵያ የሆኑ ኤርትራዉያንን ለኢትዮጵያ ያላቸዉን የተዛባአመለካከት ጠንቅቀን እናዉቃለን ሲጀመርስ ለዚህ ያደረሰን ማን ሁኖ።

ድርድ ሲደረግ በተምበርካኪነት መቅረብ ያለዉንም የሚቀጥለዉንም ትዉልድ አንገት ያስደፋል ኢትዮጵያ ምድሩ ገደል የሆነባት አገር አይደለችም ተጠምዝዘን የተቀማነዉን ጠምዝዞ የሚቀበል ትዉልድ ይመጣል እሱን ባናሰናክለዉመልካም ይመስለኛል። በተረፈ በአለሙ ዳርቻ የተበተኑት ኤርትራዉያን የሰሞኑን የዶ/ር አብይን የተለሳለሰ መልእክትና ተስፋ በመስማት ወደ ኢትዮጵያ ለመጉረፍከባድ ዝገጂት ላይ ናቸዉ። እንደ አንድ ዜጋ የሀገሬ ሁኔታ ያሳስበኛል 110 ሚሊዮን ሀዝብ በማይበቃው መሬት ላይ ቁጭ ብሎ የሚጠሉትን ባእዳን በፍቅር ማስተናገድ የሚጠበቅበት አይመስልም። ኤርትራዉያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ወዳጂነትመንፈስ አይደለም ይልቁንስ በጥንቃቄ የተሰራ የዘረፋ መረብ ዘርግተዉ ከትግሬ የተረፈዉን ለመጋጥ ነዉ የተገኘዉን እድል በመጠቀም ትግሬዎችም ኤርትራዊ ሁነዉ ለነገዉ ጥፋታችን ዋስትና ባንሰጣቸዉ መልካም ነዉስለ ሀገሩ የሚያስብ ዜጋ እንቅስቃሴያቸዉን በሚገባ ማጤን ይገባል  ዶ/ር አብይም የኤርትራን ፍቅር በልኩ እንዲያደርገው እንደ አንድ ዜጋ እጠይቃለሁ። የኢትዮጵያ መሪ በመሆንህ ክብርህሲነካ እኛም አይመቸንም እነሱ የሚያወሩት አንተ ያሰብከዉን አይደለምና ምድር ባቡር የሚያገናኝን እሰራለሁ የአዉቶብስ መንገድ እከፍታለሁ ወደቡን አድሳለሁ ፤ኤርትራዉያን በፈለጉ ጊዜ ገብተዉ የፈለጉትን ያደርጋሉ በሌለ አየር መንገድ 20% መዋእለ ንዋይ ኤርትራ አየር መንገድ ላይ አፈሳለሁ የሚለዉ አባባል ሀገርን አደጋ ላይ ከመጣሉ ባሻገር የደህንነት በጀቱም በዚህ ሚዛን በጎደለዉ ክፍት አሰራር በጣም ሊጨምር እንደሚችል ማመላከት እንወዳለ

ከዚህ ተያይዞ በሚፈሙት የድምበር ዉሎች ላይ በታሪክ እና በሚቀጥለዉ ትዉልድ ተወቃሺ እንዳትሆን ደግመህ ነገሩን ብታጤነዉ መልካም ነዉ እንላለን በእርግጥ ነገር በችኮላ  ከእጂህ አምልጧል። እዉቅ የኢትዮጵያ ምሁራንባመከቱት መሰረት ለነገሩ ልጓም ተበጂቶለት በአዋቂዎች እንዲጠና እንደ  ዜጋ እናሳስባለን። ታሪክና አለም አቀፍ ዉሎች አሰብን ለኛ ይፈቅዳሉ ነገር ግን መለስ ዘራዊ ለትግራይ ትግርኛ ለወደፊቱ ፕሮግራሙ ለወገኖቹ አሳልፎ ሰጥቶብናል ወሮበላ መሪና ወንጀለኛ ድርጅቱ አሳልፎ ቢሰጠብንም ዳግም አናነሳዉም ማለት ስላልሆነ ረጋ ብለከኢትዮጵያ ምሁራን ጋር መክረ አሰብ ወደ ኢትዮጵያ እጂ የሚገባበትን በር እንድትከፍት እናሳሳብናለን። 110 ሚሊዮን ህዝበ ጉሮሮዉ ታንቆ አካባቢዉ ሰላም ያገኛል ማለት ቀልድ ነዉ።  አንጋፋ ምሁራን ተብዬዎች ማህደር ሰብስበዉ ታሪክ አጣቅሰዉ በዚህ ሁኔታ አገርን ከመዳት ምክር ከመለገስ ይልቅ አቅጣጫ በማስቀየር በእሰጥ አገባና ከወጣቶች ጋር በብሺሺቅ ተጠምደዉ እናያለን።

ለማንኛዉም ነገሩን ለማሳጠር

1. ወንጀለኛ የህወአት አባላት በፍርድ ቁጥጥር ስር ሳይዉሉ ጊዜዉን ማራዘም የመከራ ጊዜያችንን ማራዘም ስለሆነ   ለፍርድ ሳይቀርቡ እንዳያመልጡና ባላቸዉ ገንዘብ የፍርድ ስርአቱን እንዳያዛቡ ፓስፖርታቸዉን ሰብስቦ ባስቸኳይ የፍርድ ሂደቱ እንዲከናወን ማድረግ

2. ዲራን በተመለከተ የባንዳ ልጆች ከዚህ ባንዲራ ጋር የግል ጠብ ስላላቸዉ ይህ ልሙጥ ባንዲራ የነጻነታችን ምልክት በመሆኑና በሄድክበት  ሁሉ ሰለ ባንዲራችን የህዝብን ሰሜት ስለተመለከትከዉ የህትን ባንዲራ እስከ ምልክቱ ለሚሰማማቸዉ ባንዳዎች ሸልመህ ኢትዮጵያን የሚወክል የቀድሞ ብሄራዊ ባንዲራችንን ያለምንም አርማ ማዉለብለብ

3. ክልል የተባለዉ የኢትዮጵያን ወጣት አስሮ የያዘውን አጥር መበጣጠስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች እዉነታዉንና የአንድነት ጠቀሜታዉን ማሳየት በቅርቡ በሶማሊያ እና በ ኦሮሞ የደረሰዉ መፈናቀል እንደ መቀጣጫ ተቆጥሮየኢትዮጵያ ህዝብ ሳይተላለቀ ባስቸኳይ የሚፈርስበትን መንገድ መፈለግ

4. ኤርትራን በተመለከተ የሚደረገዉ ዉል ኤርትራዉያንን ለማስደሰት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ሁኖ በአጭር ጊዜና በረጅም እይታ አገርን አደጋ ላይ የማይጥል ታሪክ ጠባሳ እንዳይተዉ በተገኘዉ የመገናኛ መንገድ ለሀገራቸዉ ትልቅ ስራ ሰሩ የኢትዮጵያ ጉዳይ ጉዳያቸዉ የሆነ በዉጭና በሀገር ዉስጥ ከሚገኙ ዜጎችን ምክር እንዲጠየ በዉሳኔዉም ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑማድረግ

5. ዛሬም ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ ኢትዮጵያን በኤርትራ እስር ቤት ታጉረዉ ይገኛሉ ከነዚህም መሀል ወጣት ተስፋዬ ስመ ጥሩ የጦሩ አባላት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህና ኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ ይገኙበታል ኮለኔል አብይ የዉይይቱ መክፈቻ እነዚህ ጓዶቹ መሆን ሲገባዉ በኤርትራኖች ቅኝት ዙሪያ ብቻ መሽከርከሩ ቅር እንዳለን እንዲያዉቀዉ ሁኖ አሁንም  በዚሀያ የሚሰቃዩት ወገኖቻችን በሰላም ወደ ሃገራቸዉ የሚሸኙበትና መንግስት የሚያገግሙበትን ሁኔታ እንዲመቻች እንጠይቃለን።

6. ከሰሞኑ ጫጫታ እንደምንመለከተዉ ሹመትን በተመለከተ መስፈሪያዉ ዘርና የድርጅት አባላነትና ክልላዊነት ሳይሆን ብቃት ሁኖ እንዲታይም እንጠቁማለን ይህ አሰራር ላለፉት 27 አመት ተሞክሮ አልሰራም ወደፊትም አይሰራም ይህን የሚፈልጉት ደካሞችና ከክልላቸዉ ወጥተዉ ለመስራት ችሎታ የሌላቸዉ ናቸዉ። በቀደመዉ ታሪካችን ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳዳሪ ሁነዋል ደጃዝማች እንቁ ስላሴ የከፋ አስተዳዳሪ ሁነዋል ዛሬም ዶ/ር አብይ ከኦሮምያ የኢትዮጵያ መሪ ሁኗል።፡ይህ በዘርና በክልል አጥር ዜጎችን የሸበበዉ አሰራር የኢትዮጵያ ወጣቶች እያነሱ እንዲሄዱ የሚያደርግ ሆን ተብሎ በትግሬ ኤሊቶች በማር የተቀባ መርዝ በመሆኑ ባስቸኳይ የሚወገድበትን መንገድ መፈለግ።

እዚህ ላይ ዶ/ር አብይና ፓርቲያቸዉ ያልፋሉ ችግሩ ችግር ሁኖ የሚቆየዉ ለኢትዮጵያና ለተከታዩ ትዉልድ ነዉ። እንግሊዝና ጀርመን በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት የኛን የማያል ጦርነት ገጥመዉ ተቆሳስለዋል ዛሬ በአዉሮፓ ህብረት አማካይነት በጋራ ይሰራሉ ነገር ግን እንግሊዞች የወደቁትን ጀግኖቻቻዉአራክሰዉ የግዛት ድምበራቸዉን አሳለፍዉ ከጀርመን ጋር የማይሆን ስራና የሚያሳፍር ስምምነት አልተፈራረሙም።፡ዶ/ር አብይም የኤርትራን ፍቅር ልጓም አበጂቶለት በሰከነ መልኩ ይመርምረው እንላለን

ዶ/ር አብይ ዛሬ በግሉ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ቢወዳደር ክርሰቲያን፤እስላም፤ወንጌላዉያንና ሴቶች የአማራ/የደቡብ/የኦሮሞ ወጣቶች ከርሱ ጋር እንደሚቆሙ በትክክል መተንበይ ይቻላል። ዶ/ር አብይ በእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተመረጠ ኢህአደግ ተብሎ ህወአት በፈጠረዉ የማፍያ ቡድን ተሸፍኖ የህወአትን ነብስ ማዳን የሚጠበቀብት አይመስልም ምናልባትም ይህ ነገር አእምሮዉ ዉስጥ ካልደረሰ እንዲያስብበት ልናመላክት እንወዳለን

እንግዲህ እንደ ተለመደዉ ለመማማር፤ለወቀሳ፤ለስድብ በዚች በኩል ድረሱኝ semere.alemu@yahoo.com

LEAVE A REPLY