በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ዕርቀ_ሰላም መውረዱ ተሰማ

በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ዕርቀ_ሰላም መውረዱ ተሰማ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ለ27 ዓመታት ለሁለት ተክፍሎ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እርቀ_ሰላም ማውረዱ ተሰማ። የሀገር ውስጥና የውጭ በሚል ለሁለት ተከፍሎ ለ27 ዓመታት የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በመጀመሪያ ውሎው፣ ዕርቅ ፈጥሮ  ከሁለት ወደ አንድ ሲኖዶስ ለመጠቃለል ስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል።

የአስታራቂው ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ለአድማስ ሬድዮ እንደተናገሩት “ዕርቁ በይፋ ተፈጽሟል” ከዚህ በኋላ የሚቀረው ዝርዝር ጉዳይና የሂደት ጉዳይ ነው ብለዋል። በመሆኑም ትልቁ ውሳኔ ዛሬ መከናወኑን ይፋ አድርገዋል።

የውጭውን ወይም መቀመጫውን በአሜሪካን ሀገር ያደረገውን ሲኖዶስ የሚመሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 4ኛ ፓትሪያርክ አቡነ መንቆሪዮስ ወደ ቀድሞ ዙፋናቸው እንደሚመለሱ ተጠቁሟል።

ጠ/ሚኒስትሩ አብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት አስታራቂ ኮሚቴውን በጽ/ቤታቸው ጠርተው ባነጋገሩበት ወቅት የዋሽንግተን ዲሲው የሲኖዶስ ዕርቀ ሰላም በቶሎ እንዲከወን አደራ በማለት መሸኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በስነ_ስርዓት ጨርሳችሁ ከተመለሳችሁ፤ በሚሌኒየም አዳራሽ ዕውቅና የሚሰጥ ወይም የምስጋና ፕሮግራም እንደሚዘጋጅ መጠቆማቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY