ጣና ሐይቅ ጤንነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

ጣና ሐይቅ ጤንነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

ጎበዝ የጣና ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል:: ከዚህ በፊት የተደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ ሊባል በሚችል ደረጃ የተከናወነ ውሽልሽል ነገር ሆኖ እያለ አሁንም በጣና ስም ገንዘብ መሰብሰቡ ቀጥሏል:: ከዚህ በፊት በተሰበሰበውም ሆነ አሁን እየተሰበሰበ ባለው ገንዘብ ምንም እርባና ያለው ስራ አልተሰራም እየተሰራም አይደለም:: ያለው እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ለዚህ ችግር ፊትአውራሪነት እራሳቸውን “አለም ዓቀፋዊ” አድርገው የሾሙ ቡድኖች ግን አሁንም መረጃ ከህዝቡ እየደበቁ መሽሎክለካቸውን ቀጥለዋል::

ጉዳዩ አይደለም በአንድ የመንደር ውሽልሽል ቡድን ሊፈታ ቀርቶ አለም አቀፍ ትኩረት ተሰጥቶትንኳ ከተቃለለ እድለኞች ነን:: አሁንም ቢሆን ችግሩን አሳንሰውና አጥበው በማሳየት ለራሳቸው እንቅስቃሴ እንዲመች የሚጥሩ ሃይሎች ስለሰበሰቡት ገንዘብ: ከዚህ በፊት ስለተገዙ ማሽነሪዎች ያለበት ደረጃና ስለጠቅላላ አቅማቸው እውነቱን ለህብረተሰቡ መግለፅ አለባቸው:: እርሜን ቢድሩኝ እግሬን ሰበሩኝ እንዲሉ እርማችን የአካባቢያችን ችግር አድቮኬት ብናደርግ የውሃችንን ነገር ውሃ አስበሉብን:: አሁንም ቢሆን መንግስት የጣናን ጉዳይ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ ሊሟሟትለት ይገባል::

ከዚህ በፊት የተገዙ ማሽኖች ጭራሽ በቂ አቅም የሌላቸው በቂ ጥናትም ተደርጎባቸው ያልተገዙ በመሆናቸው አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም:: ሊሰጡም አይችሉም:: ዝቅተኛ የፈረስ ጉልበት ያላቸውና ቀድሞውንም እንደጣና ላለ ጥልቅ ሃይቅ ዲዛይን የተደረጉ አይደሉም:: ሌላው ግልፅ ሊሆን የሚገባው ነጥብ ደግሞ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ከዲያስፖራው በተሰበሰበው ገንዘብ ምንም አይነት ማሽነሪ አልተገዛም:: ከዚህ በፊት በግሎባል ኳልዢን በኩል ተገዝቶ አገር ቤት የገባው ማሽነሪ እስራኤልና አትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰበሰቡት ገንዘብ የተገዛ ነው :: እሱም ቢሆን ሮንግ ማሽነሪ ስለሆነ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም:: ለማስረጃ ያክል ከታች ያለውን ቪዲዮ ተመልከቱልኝ:: ዋሽንግተን ዲሲ በተሰበሰበው ገንዘብ ሁለት ማሽነሪዎች ለመግዛት ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ምንም የተደረገ ነገር የለም:: ገንዘብ ስብሰባው ግን አሁንም ቀጥሏል:: ከዚህ በፊት በጎንደር ዩንቨርሲቲ ተሰራ የተባለው ማሽነሪም ፌል አድርጏል::

አሁን ለጊዜውም ቢሆን ትልቅ ተስፋ የምናደርገውና እኔም እራሴ በአካል ተገኝቼ እንደጎበኘሁት በሙላት ባሳዝነው ኢንጅነሪንግ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ግዙፍ ማሽነሪ ነው:: ስለዚህ ፕሮጀክት በቅርብ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት እሞክራለሁ:: በተረፈ የጣና ጉዳይ በዚህና በመሳሰሉ መውተርተሮች የሚቀረፍ እንዳልሆነ በመረዳት እንደገና የጣናችንን ጉዳይ መንግስታዊ ትኩረት እንዲያገኝ ጉትጎታችን መቀጠል አለበት:: ችግሩን አሳንሳችሁ ለማሳየትና እራሳችሁን የጉዳዩ ብቸኛ ተጠሪ ለማድረግ የተሰለፋችሁ ቁጭ ይበሉዎች ደግሞ የሰበሰባችሁትን ገንዘብ ለታለመለት አላማ አውሉና ከጣና ፊት ገለል በሉ::

ጋዜጠኞች: አልቲቪስቶች: ሃቀኛ ሙህራንና ቀናኢ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እባካችሁ ጉዳዮ በፌዴራል መንግስት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ በጎአድራጊ ድርጅቶች ትኩረት እንዲሰጠው እርብርብ እናድርግ::

በእንቅርት ላይ እንዲሉ በጣና ሃይቅ ሌላ መጤና ተስፊ አረም መከሰቱም ተዘግቧል :፡

/ኑረዲን ኢሳ/

LEAVE A REPLY