/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ ኦማር በራሳቸው ፈቃድ ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸውን ቢቢሲ ሶማሊኛ ዘገበ።
እንደ ቢቢሲ ሶማሊኛ ዘገባ ከሆነ በአቶ አብዲ መሃመድ ኦማር (አብዲ ኢሌ) ቦታአቶ አህመድ አብዲ መሀመድ አዲሱ የኢትዬጵያ_ሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾመዋል።
ሶማሌ ክልል ከዛሬ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በመከላከያና ፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ስትሆን በጅጅጋ ከተማ አንፃራዊ መረጋጋት እንደተፈጠረ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።