ሀምሌ 25/2010 ዓም አክሱም ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ አማራ ተማሪዎች ተደብድበዋል። በአክሱም፣ መቀሌና ሌሎችም የትግራይ ትምህርት ቤቶች ድብደባ፣ ዛቻና ስድብ እንደሚደርስባቸው፣ በማንነታቸው ጥቃት እንደሚፈፀምባቸው ገልፀዋል።
በዚህም ምክንያት በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት መቀጠል ለህይወታቸው አስጊ በመሆኑ አክሱምና መቀሌ ይማሩ የነበሩ 25 ያህል የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ተመልሰዋል።
ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ድብደባ፣ ዛቻና በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሲሆን መቀሌ ከተማ ውስጥ ዛሬ ሀምሌ 30/2010 ዓም አንድ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ደርሶበታል። አክሱም ዩኒቨርሲቲ ይማር የነበረ አንድ አማራ ተማሪም ተገድሏል ተብሏል።
በሌላ በኩል የትግራይ ክልል መንግስት በአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የትግራይ ተማሪዎችን ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እየመደበ መሆኑ ተገልፆአል። ከአክሱምና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት አቋርጠው የተመለሱ 25 አማራ ተማሪዎች ወደ አማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመለሱ ነገ ነሃሴ 1/2010 ዓም ለአማራ ክልል መንግስት ማመልከቻ ያስገባሉ።