የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ሶማሌ ክልል እንዲገባ ታዘዘ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ሶማሌ ክልል እንዲገባ ታዘዘ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሀገር መከላከያ ሰራዊትና  ፌዴራል ፖሊስ ወደ  ሶማሌ ክልል ገብቶ ፀጥታ እንዲያስከብር ታዘዘ። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፤ የክልሉ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የፀጥታ ሀይሉ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም የማስከበር ስራውን እንዲሰራ መታዘዙን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፀጥታ የማስከበር ስራ እንደሚጀምር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ተናግረዋል።

በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች የታጀቡ ብዛት ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ከሰዓት ወደ ጅጅጋ ከተማ በመግባት ላይ እንደሆኑ የተለያዩ አካላት እየገለጹ ነው። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማው ሲገቡ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እንዳልገጠማቸውም ተገልጿል።

ትናንት ማታ የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ(ከደቂቃዎች በሗላ የተነሳ) እንዳሰፈረው በግጭቱ 45 ሰዎች እንደሞቱና በርካቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልፆ ነበር።

ነገር ግን የአይን እማኞች እንደሚገልፁት የሟቾች ቁጥር ከዚህም እንደሚልቅ እየገለፁ ነው።

LEAVE A REPLY