ኦህዴድ መጠሪያውን ወደ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ መቅረቡ ተገለፀ

ኦህዴድ መጠሪያውን ወደ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ መቅረቡ ተገለፀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያውን ወደ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ መቅረቡ ተገለፀ።

የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፤ አህዴድ የስያሜና የአርማ ለውጥ ለማድረግ ሀሳብ ቀርቧል። በዚህም መሰረት አዲሱ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” እንዲሆን ሀሳብ መቅረቡን አቶ አዲሱ በፌስ ቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ኦህዴድ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን አርማም ለመቀየር ሦስት አርማዎች በአማራጭነት መቅረባቸውን ገልጸዋል።

ኦህዴድ በያዝነው የነሐሴ ወር ድርጅታዊ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ የተገለጸ ሲሆን በጉባዔውም ኦህዴድ የደረሰበትን የትግል ምዕራፍ ከግንዛቤ በማስገባት የስያሜ፣ የዓርማና ድርጅታዊ መዝሙሩን በአዲስ ሊቀይር እንደሚችል ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY