በኮምቦልቻ ከተማ መስጊድ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

በኮምቦልቻ ከተማ መስጊድ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ተቅዋ በተባለ መስጊድ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ከ11 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና እርዳታ መላካቸውን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ጠቆሙ። ከተጎጅዎች መካከልም  የ14 ዓመት ታዳጊ እንደሚገኝበት ታውቋል።

ባለፈው ወርም በደሴ ከተማ እንዲሁ በመስጊድ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው የሚታወስ ነው።

 ዘሪሁን ገሰሰ በስፍራው በመገኘት የሚከተለውን ዘግቧል።

______

“ዛሬ ጠዋት ከሱብሂ ሰላት በኃላ፤ በኮምቦልቻ ከተማ ተቅዋ መስጂድ በተፈጠረ የእርስበርስ ግጭት በርካታ ሠዎች ተጎዱ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከአሁን በፊት መስጂዱን ተቆጣጥረውት በነበሩትና ከመንግስት ድጋፍ አላቸው በሚባሉት የአህባሽ አስተምህሮ አራማጆችና ሱኒይዎች መካከል ሲሆን፤ ለአህባሾች <<መስጂዳችንን አስረክቡን!>> የሚል ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩት ሙስሊሞች፤ ከሱብሂ ሰላት በኃላ በመስጂድ ውስጥ የነበሩ ሠዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ፤ እስካሁን 11 ሠዎች ክፉኛ ተጎድተው ወደደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በአንቡላንስ እንደሄዱና በኮምቦልቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ውስጥም በርካታ ተጎጂዎች እንደሚገኙ ተሠጋግጧል፡፡ ከተጎጂዎቹ ውስጥ አብዛኛዎቹ ከ14-18 አመት ያሉ ታዳጊዎች ሲሆኑ አንድ የ14 አመት ልጅም በተመሳሳይ በፌሮ ብረት ተመትቶ ክፉኛ እንደተጎዳ ለማወቅ ችያለሁ፡፡

ጉዳቱን አድርሠዋል የተባሉ ከ10 የሚልቁ ወገኖች በኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው፡፡ በርካቶች ደግሞ እንዳልተያዙም ከአካባቢው ምንጮች ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ የአድማ ብተና ሠራዊትና ፖሊስ አካባቢውን የማረጋጋት ስራ እየሠራ ነው፡፡ በአሁኑ ሠአት በአካባቢው መጠነኛ መረጋጋትም ተፈጥሯል፡፡ በመስጅዱ ውስጥ ክላሽ እንኮቭ መሳሪያ ተገኘ የተባለው ግን ከወሬ በዘለለ በመረጃ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡”

LEAVE A REPLY