/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡-ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም፣ታማኝ በየነና ኦባንግ ሜቶ የተካተቱበት የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ አስተባባሪ ኮሚቴ መቋቋሙን የጠላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልጸዋል።
የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ኮሚቴ 15 አባላት ያሉት ሲሆን በተለያየ ሙያ የተሰማሩ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።የኮሚቴው አባላት ስም ዝርዝርም፦
- ፕሮፌሰር አለምአየሁ ገብረማርያም – የምክር ቤቱ ሊቀመንበር
- ዶክተር ብስራት አክሊሉ
- አቶ ገብርኤል ንጋቱ
- አቶ ካሳሁን ከበደ
- ዶክተር ለማ ሰንበት
- ወይዘሮ ሉሊት እጅጉ
- ዶክተር መና ደምሴ
- ወይዘሮ ሚሚ አለማየሁ
- አቶ ሚኒልክ አለሙ
- አቶ ኦባንግ ሜቶ
- አቶ ሮብሰን ኢታና
- አቶ ታማኝ በየነ
- አቶ ተሽታ ቱፋ
- አቶ ይሄነው ዋለልኝ እና
- አቶ ኤሊያስ ወንድሙ የምክር ቤቱ አባላት ሆነው መመረጣቸውን አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ዛሬ አስታውቀዋል።