ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ...

ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ ገለፀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡-በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው የነበሩት ኮሚሽነር ግርማ ካሳ እና 11 የፖሊስ አመራሮች ያቀረበቱ የዋስትና ጥያቄ በተመለከተ ዐቃቤ ህግ በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ገለጸ።

ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው ቢከታተሉ እንደማይቃወም መግለጹን ተከትሎ ፍርድ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ ሰኔ 16/2010ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት ቦንብ በመጣልና በማቀናጀት በዕለቱ ተጠርጥረው የተያዙ አምስት ሰዎች ላይ መደበኛ ክስ ለመመስረት ፌዴራል ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለአቃቤ ህግ መስጠቱም የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY