/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በአዳማ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች መጠለያቸው በእሳት እየተቃጠለ ነው ተባለ። በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ተፈናቃዮች በአዳማ ከተማ መጠለያ ተሰርቶላቸው እንደሚኖሩ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በፈጠሩት ግጭት ምክንያት መጠለያቸው በመቃጠል ላይ መሆኑ ታውቋል።
በተለይም ካለፈው ዓመት ወዲህ ከሶማሌ ክልል ከአንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉ ሲሆን በሐረር፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ (ናዝሬት)፣ አዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎችም መጠለያ ተሰርቶላቸው በጊዜዊነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።