የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በከተማ ደረጃ አመራሮችን በአዲስ መልክ አዋቅሮ የሪፎርም ስራውን እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ለማድርስ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
ከዘረዘሯቸው ጉዳዮች መካከል የመሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች አንዱ የሪፎርም አካል እንዲሆን አጽእኖት የተሰጠው ጉዳይ ሲሆን በከተማው የሚገኘውን መሬት ኦዲት የማድረግ ስራ አንዱ ነው። በመሆኑም ይህን የተጀመረውን ሪፎርም አጠናክሮ ለማስቀጠል ያስችል ዘንድ ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን የአገልግሎት አይነቶች በአጭር ግዜ ውስጥ የቅድመ ዝግጅት ስራችንን ካጠናቀቅን በኃላ የምንሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ለጊዜው እንዲቆሙ የተወሰነባቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦
- የግል ኢንዱስትሪ አልሚዎች የመሬት ጥያቄ
- በይዞታ አስተዳደር የሽግግር ግዜ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ውስጥ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል (የሰነድ አልባ እና አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ይዞታዎች መስተንግዶ )
- መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ማህበራት መስተንግዶ አገልግሎቶች የቅድመ ማጣራት ስራ እስቂጠናቀቅ ድረስ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለጽን፣ ህብረተሰቡ የህዝብ እና የመንግስት ንብረት የሆነውን መሬት ከብክነትና ከህገወጦች እንዲከላከል ከንቲባ ጽ/ቤቱ በአክብሮት ይጠይቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
ነሐሴ 2010 ዓ.ም