/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡-ከጅቡቲ በመመለስ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሀክምና ለመስጠት 4 የድንገተኛ ህክምና ጣብያዎች በድሬዳዋና አካባቢው መቋቋማቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር አሚር አማን አስታወቁ።

ከተመላሽ ኢትዮጵያዊያኑ መካከል 74 የድንገተኛ(AWD) ህሙማን ታክመው 24ቱ ማገገማቸውን እንዲሁም ቀሪዎቹ  ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ሚንስትሩ ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት በድሬ ዳዋ ከተማ በተነሳ ግጭት ከአምስት በላይ የጅቡቲ ዜጎች መገደላቸውን ተከትሎ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የሀገሪቱ ፖሊስ ከፍተኛ በደል እያደረሰባቸው መሆኑን መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱ መረጃዎች ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY