የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን...

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ስር ያዋለው የጦር መሳሪያ በነዳጅ ቦቴ አማካኝነት ሲዘዋወር መሆኑ ገልጿል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በቁጥጥር ስር የዋለው 1051 ሽጉጦችና መጠናቸው ያልታወቁ ጥይቶች መያዛቸው ታውቋል።

 በሌላ በኩል የፌዴራል ፖሊስ እንዳስታወቀው ዶላር በጥቁር ገበያ ሲመነዝሩ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች 8700 የአሜሪካን ዶላርና 600 ሺህ ብር እንደያዙ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ቤት ሲገባ እንዲሁም  የውጭ ገንዘቦች ከሀገር ሲወጡ በተደጋጋሚ መያዛቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY