በኦሮሚያ ክልል በህገ_ወጥ ተግባራት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልል በህገ_ወጥ ተግባራት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ህገ_ወጥ ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ከ500 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ህግና ስርዓትን በመተላለፍ በንፁሃን ዜጎች ላይ በህይወትና የንብረት ላይ ውድመት ያደረሱ መሆናቸውን የፀጥታ ቢሮው አስታውቋል።

በጉጂ ዞን በቄሮ ስም መሬት ወረራ የፈጸሙና ያስፈጸሙ፣ ህገ ወጥ ኬላ በማቋቋም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ያስተጓጎሉ፤ መንግስት የሚሰጠውን ስልጣን ሁሉ በቄሮ መረጋገጥ አለበት በሚል ያነሳሱ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

በባሌ ዞንም የእርሻ ኢንቨስትመንት ያደናቀፉ፤ በቡኖ በደሌ ዞን በአካባቢው የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆችን የቡና እና የጫት ምርቶች የመነጠሩ እንዲሁም በጂማ ዞን የሰዎችን ቡና በመመንጠር ብሎም ቡዳ ነው በሚል ሰው የገደሉና ያስገደሉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

LEAVE A REPLY