/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢትዮ_ቴሌኮም በስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተቋሙ በስልክ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህ መሰረት የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የ43 በመቶ፣ የስልክ ድምፅ ላይ የ40 ከመቶ እንዲሁም አጭር የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት ላይ የ43 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል። የታሪፍ ቅናሹ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።
የብሮድባንድ ሲም ካርድ ሽያጭ ለጊዜው እንደተቋረጠ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ባንኮች፣ ሆቴሎችና ሱፐርማርኬቶች ጋር አጋርነት በመፍጠር የብሮድ ባንድ ሲም ካርድ ሽያጭ እንዲያከናወን ይደረጋልም ተብሏል።
የታሪፍ ቅናሹን ተከትሎም በደቂቃ 83 ሳንቲም የነበረው የሞባይል ስልክ ጥሪ አገልግሎት ወደ 50 ሳንቲም ዝቅ እንዲል ሲደረግ፤ከዚህ ቀደም በ35 ሳንቲም ይገዛ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት(ባንድል) አገልግሎት 43 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት ወደ 23 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን በዛሬው መግለጫ ተጠቅሷል።