ሰበር ዜና፦ አቶ በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ታገዱ

ሰበር ዜና፦ አቶ በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ታገዱ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ካሳ ከድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱን አስታወቀ። አቶ በተከትና ታደሰ ካሳ ከድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴው እንዲታገዱ የተደረገው የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡ እና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሞቴ ለሁለት ቀናት ባደረገው ስብሰባ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፤ ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን መመሪያም መሻሩን አስታውቋል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር አይሳተፍም ተብሏል።

 አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ካሳ የድርጅቱ መስራችና ለረጅም ዓመታት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ሲሆን እስከ ሚቀጥለው መስከረም ወር ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑን ኢቲቪ በሰበር ዜናው ዘግቧል። ኢቲቪ በነገው ዕለትም ዝርዝር ማብራሪያ ይዞ እንደሚቀርብም አስታውቋል።

አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ባለፉት 27 ዓመታት በተለይም በአማራ ክልል በተፈጸመው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶ ጥሰቶች ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሚሆኑ ሲገለፅ መቆየቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY