ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ  እንደገለጹት፤ መራሂተ መንግስት ሜርክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን በመግለጽ እንኳን ደስ ያልዎት ማለታቸውንም አቶ ፍፁም ጨምረው ገልጸዋል።

መራሂተ መንግስቷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው በአፍሪካና በአውሮፓ ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ የጋበዟቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብዣውን  መቀበላቸውን አረጋግጠውላቸዋል።

መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ሲወያዩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል

LEAVE A REPLY