/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ በርሃ ያለውን ወታደራዊ ካምፕ በመዝጋት ወታደሮቹን ወደ ኢትዮጵያ እያስገባ መሆኑ ተገለጸ። የንቅናቄው ወታደሮች በሁመራ በኩል በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባትት ጉዞ መጀመራቸውንም የተለያዩ የኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ከ200 በላይ የሚሆኑ አመራሮቹ በሚቀጥለው እሁድ ጳጉሜ 4 ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡ ሲገለጽ ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነፍጥ በማንሳት በውጭ ሀገራት የሚገኙ ተቃዋሚ ሀይሎች ወደ ሀገራቸው ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ጥሪ ማድረጋቸውን ተክትሎ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራትና ታዋቂ ግለሰቦች ወገ ሀገራቸው እየገቡ እንደሚገኙ ይታወቃል።