የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ዘጠኝ ባለሙያዎች መታሰራቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ዘጠኝ ባለሙያዎች መታሰራቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስጣን እንደገለጸው “አለም አቀፍ በረራዎችን ለማደናቀፍ የሞከሩና የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን የስራ ማቆም አድማን ሲያስተባብሩ እንዲሁም ሲመሩ ነበር ያላቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

 የፌዴራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ አይፎክሩ ለፋና እንደገለጹት፤ግለሰቦቹ የበረራ ሂደቱን ለማስተጓጎል በተለይም ከውጭ ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸዋል።ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ ግለሰቦቹ በፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና በአሁኑ ወቅትም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

 ቁጥራቸው ከ120 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የደመወዝ፣የጥቅማጥቅና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

 የኬንያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማኅበር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ሰራተኞቹ የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው በአካባቢው የአየር በረራ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ተፈጥሯል ማለቱ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY