ሳውዲ አረቢያ በውጭ ሀገር ሰራተኞች ላይ የምጥለው ክፍያ አለመኖሩን አስታወቀች

ሳውዲ አረቢያ በውጭ ሀገር ሰራተኞች ላይ የምጥለው ክፍያ አለመኖሩን አስታወቀች

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ሳውዲ አረቢያ በውጭ ሀገር ሰራተኞች ወደ ሀገራቸው  ከሚልኩት ገንዘብ (ሬሚታንስ) ላይ ክፍያ እንዲፈጽሙ ግዴታ ልትጥል የተባለው ወሬ ሀሰት መሆኑን ገለጸች።

  ማንኛውም የውጭ ሀገር ሰራተኛ ወደ ሀገሩ በሚልከው ገንዘብ ላይ ተጨማሪ ክፍያ እንደይጠየቅ የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር መግለፁን ሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ እየተወራ ያለው አሉባልታ መሰረተ ቢስ ነው፤ ይልቁንም ሀገራችን ነፃ  የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ትደግፋለች ማለቱን በዘገባው ተጠቅሷል።

የሳውዲ መግስት ፍላጎት ሁሉም ሰው ገንዘብ ሲያዘዋውር ህጋዊ መስመሮችን ተከትሎ እንዲሆን እንጂ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ጫና መፍጠር ፍላጎታቸው አለመሆኑም ተገልጿል።

 በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ከ10 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ሰራተኞች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 38 ቢሊዮን ዶላር ወደየ ሀገሮቻቸው መላካቸውን መረጃ ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY