የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ዛሬ ከሰዓት በሗላ ከአስመራ ወደ ጁቡቲ የተጓዙት የሦስቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ከጅቡቲ አቻቸው እንዲሁም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል።

 የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ኢሴ የተካተቱበት ውይይትም ለበርካታ ዓመታት ኤርትራና ጅቡቲ ሲወዛገቡበት የቆየውን በሁለቱ ሀገራት ደንበር አካባቢ በሚገኘው ዱሜራ ደሴት ጉዳይ ላይ መወያየታውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ  የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላምን ለማረጋገጥ ያለመ ውይይትም ማድረጋቸው ታውቋል።

 የሦስቱ ሀገራት መሪዎች በአስመራ ከተማ በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ግንኙነት ለመስፍጠር የተስማሙ ሲሆን የኤርትራ እና ጅቡቲ የድንበር ውዝግብ  እልባት እንዲያገኝ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተስማምተዋል።

 የኢትዮጵያ፣ኤርትራ እና ሶማሊያ ተብብሮ ለመስራት ያሳዩት ተነሳሽነት ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ሲገለፅ፤ በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ባህል እና ፀጥታ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ እንዲነሳ ሲጠይቁ ጅቡቲ በበኩሏ መቃወሟ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY