የአዲስ ዓመት ዋዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ ፕሮግራም ተካሄደ፤ 9ሺህ እስረኞች ተፈቱ

የአዲስ ዓመት ዋዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ ፕሮግራም ተካሄደ፤ 9ሺህ እስረኞች ተፈቱ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የ2011ዓ.ም መግቢያ አዲስ ዓመት ዋዜማን ምክነያት በማድረግ በሚሊኒየም አዳራሽ ፕሮግራም ተካሄደ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመድን ጨምሮ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ ከፍተኛ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የኪነ_ጥበብ ሰዎችና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተገኙበት ደማቅ የአዲስ ዓመት አቀባበል ፕሮግራም ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የክልል ር/መስተዳድሮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አቅርበዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት “አዲስ ዓመትን እየተቀበለ በአሮጌው አስተሳሰብ መሄድ ምኑን አዲስ ዓመት አከበረው? በመሆኑም በአዲሱ ዓመት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከእርስ በእርስ መናቆር ወጥተው ለሀገር እድገት የሚተጉበት፣ የመንግስት ባለስልጣናት የስልጣን ወንበር ለማገልገል እንጅ ለመግዛት አለመሆኑን መረዳት አለባቸው።”በማለት ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትር አብኢ ያለፈው አሮጌው ዓመት ኢኮኖሚያችን ለቀውስ የተዳረገበት፣ ወጣቶች የተሰደዱበት፣ ዜጎች በእስር የተሰቃዩበት አስቸጋሪ ዓመት ነበርም ብለዋል።

 ዶክተር አብይ የሚቀጥለው አዲስ ዓመት ሚዲያዎች 4ኛ መንግስት መሆናቸውን በተግባር ማሳየት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

በሌላ በኩል አዲሱን ዓመት አስመልክተው የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ክልሎች በርካታ እስረኞችን በይቅርታ መፍታታቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም ኦሮሚያ 5325፣ አማራ ከ3427፣ ጋምቤላ 400 እንዲሁም ቤንሻንጉል ጉምዝ 188 በድምሩ ከ9340 እስረኞች በላይ ከእስር ቤት መፈታታቸው ተገልጿል።

LEAVE A REPLY