የቴዲ አፍሮ ዝግጅት በወቅቱ ግርግር ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

የቴዲ አፍሮ ዝግጅት በወቅቱ ግርግር ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ዝግጅት ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተገለጸ። ነገ ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ለሚቀጥለው ሳምንት መተላለፉን የአርቲስቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ እንደገለጹት ኮንሰርቱ ለሚቀጥለው ሳምንት እንዲተላለፍ የተደረገው በአዲስ አበባ ከተማ ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በታላቅ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረ እና ከረጅም ጊዜ በሗላ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሲሆን ለኮንሰርቱ መግቢያ ካርድ ተዘጋጅተው የነበሩ ቲኬቶች በ500 ብር ተሽጠው ማለቃቸውንም መረጃዎች አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY