/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በነገው እለት ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ያለምንም የጸጥታ ችግር እነዲከናወን የከተማ አስተዳደሩ ስላደረገው ቅድመ ዝግጅት መግለጫ ሰተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የከተማዋ ነዋሪ ከሀገር ውጭ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና ቡድኖችን በሰላማዊ መንገድ ሲቀበል እንደነበረው ሁሉ የኦነግ አመራር የሆኑ ወንድሞቹንም በፍጹም ጨዋነት እንዲቀበል ጠይቀዋል፡፡
አቀባበሉንና ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ በህዝብ መካከል አላስፈላጊ ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉ አካላት ላይም አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚውሰድ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ነዋሪም የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል ከ ኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ወንድሞቹን በእንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በፍቀር ተቀብሎ እንዲያሰተናገዳቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ም/ከንቲባው ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን፣ ከፀጥታና ደህንነት፣ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ውይይት ማደረጋቸው ታውቋል።
በአዲስ አበባ የተከሰተው ግጭት ዛሬም በአንዳንድ ቦታዎች የቀጠለ ሲሆን በቡራዩ የግለሰቦች ንብረት እየተዘረፈና እየወደመ መሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በከማል ገልቹ የሚመራው የኦነግ አንድ ክንፍ 1300 ወታደሮቹ ከኤርትራ በዛላንበሳ በኩል አቋርጠው አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገልጿል።