ዘውገኝነት – ዳግማዊ ዘመነመሳፍንትነት /አዲስ ጀምበር/

ዘውገኝነት – ዳግማዊ ዘመነመሳፍንትነት /አዲስ ጀምበር/

ኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ባልነበራት ወቅት ልግዛ ላስገብር ባዮች ኢትዮጵያን በመሳፍንት ግዛት ተቀራመቷት፡፡ በስልጣን ግብግቡ ሂደት አሸናፊው መስፍን ግዛቱን አስፋፍቶ ንጉሰ ነገስት ሆናል፡፡ በማዕከላዊ መንግስት መጠናከር የተወገደው ዘመነ መሳፍንት አገዛዝ አልገዛም አልገብርም ያለውን ሁሉ የራሱን አካባቢ ጨምሮ በሃይል ከማንበርከክ አልፎ እንደ ዳግማዊ ዘመነ መሳፍንት ዘረኛ እና አክራሪ ስላልነበረ ብሄርም ሆነ እምነት ተኮር ዘመቻ አልፈጸመም፡፡ ቀዳማዊ እና ዳግማዊ ዘመነ መሳፍንታትን ሚያመሳስላቸው ኢትዮጵያን መቀራመታቸው ሲሆን የሚለያያቸው ግን ቀዳማዊ በብዛት ዳግማዊ በብሄር ኢትዮጵያን መሸንሸናቸው ነው፡፡

ቀጥሎ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ምሰረታ የጠፋው ህይወት፤ የወደመውሃብት፤ ንብረት፤ የደረሰው በደል እና ግፍ ዛሬ በኢትዮጵያ የሚታየውን የማያግባባ ታሪክ እና ትርክት ወለደ፡፡ አስገራሚነቱ የማያግባባ የታሪክ እና የትርክት ልዩነት መፈጠሩ ሳይሆን የኢትዮጵያ የተለየ ክስተት ሆኖ መታየቱ፤ አሸናፊውን በዳይ ተሸናፊውን ተበዳይ አድርጎ መፈረጁ፤ተሸናፊው አሸናፊ ፤አሸናፊው ተሸናፊ ቢሆኑ ኑሮ ዛሬ የሚታየው የፖለቲካ ችግር አይፈጠርም ነበር ተብሎ መታሰቡ ፤የኢትዮጲያ ሀገረ መንግስት ምስረታ የልግዛ ላሰገብር የስልጣን ግብግብ እንጅ የህዝብ ለህዝብ ግጭት እንዳልነበረ ግንዛቤ አለመወሰዱ ማንም ነገሰ ማን ሁሉም ብሄረሰቦች አንባገነኖችን ተሸከሙ እንጅ እኩልነትን ነጻነት እና ፍትህ እንዳላገኙ አለመረዳቱ ነው፡፡

ሀገረ መንግስታት ምስረታ በጥቅሉ ሲታይ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ሂደት እና ውጤት እንዳላቸው ታሪክ ያሳያል፡፡በዚህ ሂደት በሃገሮች መካከል የታየው ልዩነት ቀጣይ ህይወታቸውን ያደራጁበት እና የመሩበት መንገድ ነው ፡፡እንደ ኢትዮጵያ ካሉ ሀገሮች በቀር ሌሎች የደረሰውን ሁሉ እንዳለ ተቀብለው እና እውቅና ሰጥተው ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ የፖለቲካ ስርዓት መስርተው በእኩልነት እና በአንድነት የጋራ ህይወታቸውን መስርተዋል፡፡ለዚህ ሂደት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ከግል ፍላጎት ይልቅ የሀገርን እና የህዝብን ፍላጎት ያስቀደሙ ፤የግል የወል እና የጋራ መብቶች በእኩልነት የሚከበሩበት ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት እንዲመሰረት ጥረት ያደረጉ ምስጋና ይግባቸው እና የፖለቲካ ሊህቃን ምሁራን እና ሀገር ወዳዶች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄረሰቦች እና እምነት ተከታዮች ሀገር ብትሆንም ብሄረሰቦች የማንነት ልዩነት ሳይገድባቸው የዘመናት የጋራ እሴታቸውን ፤ባህላቸውን፤ ታሪካቸውን እና ማንነታቸውን ይዘው የጋራ ህይወታቸውን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ አብረው ኑረዋል፡፡በ 1960 ዎቹ ብቅ ያሉ የብሄር ድርጅቶች የብሄር ማንነትን አጎሉት ፤ከመገንጠል በእኩልነት እና በነጻነት አብሮ እስከመኖር ድረስ ለጠጡት፤ተወዛገቡበት፤ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያን ህልውና ተፈታተኑበት፡፡የዘውገኞች የፖለቲካ ፍላጎት መጠቀሚያ የሆነው የታሪክ እና ትርክት ልዩነት መዘዝ ኢትዮጵያን የት እንዳደረሳት የወያኔ የ 27 ዓመት ዘረኛ አገዛዝ ህያው ምስክር ነው፡፡

ወያኔ ያቀጣጠለው የዘር ግጭት ሚሊዮኖችን አፈናቅለ፤ የሺህዎችን ህይወት ቀጠፈ፤ ሰው ተዘቅዝቆ ወደተሰቀለበት ተወግሮ እና ተቃጥሎ ወደ ተገደለበት ደረጃ አደረሰ፡፡ ወያኔ የዘረኝነት ቫይረሱን ማሰራጨት እና የቫይረሱ ተሸካሚ ዘውገኞችን ማፍራት ቢሳካለትም የስልጣን አድሜው ግን ተጨናገፈበት፡፡ወያኔ ትናንት የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጽዳት እንዳልፈጸመ ፤የሀገርን ሀብት ንብረት እንዳልዘረፈ የሌላን ማንነት ገፎ በትግራዊነት እንዳላጠመቀ፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሺህዎችን እንዳልማገደ ፤ወዶ እና ፈቅዶ የአልጀርስን ስምምነት እንዳልተቀበለ፤ ዛሬ ግን ከቤተመንግስት ሲወጣ ስለ እኩልነት ፤ተባብሮ ስለመኖር ወይም መበታተን፤ ስለብሄር ተኮር ጥቃት ወንጀልነት ስለህግ የበላይነት መከበር፤ ስለፍትህ እና ዲሞክራሲ፤ ስለ ሃገር ሉዐላዊነት መከበር ይጮሃል፡፡

በኢትዮጵያ ዛሬ ለደረሰው ሰብዐዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ተጠያቂ ዘረኛ ቫይረስ አምጪው ወያኔ ብቻ ሳይሆን የቫይረሱ ተሸካሚ የሆኑት ዘውገኞችም ጭምር ናቸው፡፡ በኦሮሞ ስም ኦህዴድ፤ኦፌኮ፤ ኦዲግ፤ ኦነግ፤ ኦተነግ፤ በአማራ ስም ብአዲን፤ አብን፤ መአህድ፤ አዲሃን፤ ሞረሽ አማራ ወገኔ ፤ የተባሉ የብሄር ድርጅቶች ተቋቁመዋል፡፡

የኦሮሞዎቹ የኦሮሞ ብሄረሰብን መብት እና ነጻነት ለማስከበር፤ የአማራዎቹ የአማራ ብሄር እየደረሰበት ያለውን ብሄር ተኮር ጥቃት ለማስቆም በሚል እንደተመሰረቱ ይነገራል፡፡ ከጀርባቸው ሌላ ፍላጎት ከሌለ በቀር እኩልነት፤ ነጻነት፤ እና ፍትህ የሚከበርበት ፤ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ቢመሰረት የሁለቱም ችግር በቀላሉ ይፈታል፡፡ የፖለቲካ አደረጃጀትም ከብሔርና እምነት ወደ የሓሳብ የበላይነት ወይም አይዲዮሎጂ ይሸጋገራል፡፡ ተፎካካሪዎችም ለሕዝብ ዳኝነት ወደምርጫ ውድድር ይገባሉ፡፡

እንደሚባለው ፍላጎታቸው የብሄራቸውን ክልል በዘውገኛ መሳፍንት ግዛት ተቀራምቶ በአሸናፊነት የወጣው ዘውገኛመስፍንግዛቱን ለማስፋፋት ወደ ሌሎች ብሄሮች ክልል መዝመት ከሆነ ቢቀር ይሻላል ምክንያቱም ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለቸው ዘጠና ብሄረሰቦች መካከል የሚደረግ የእርስ በእርስ ጦርነት ኢትዮጵያን እና ህዝበዋን እንደሚያነድ ወደሶስት ሚሊዮን ህዝብን ያፈናቀለው ብዙሽዎችን የገደለውበብዙ ሚሊዮኖች ብር የሚገመት ሃብት ንብረት ያውደመው የጌዲዮ እና ኦሮሞ፤ የኦሮሞ እና የሶማሌ፤የእርስ በእርስ ግጭት ብቻ ትልቅ የማንቂያ ደወል ነው፡፡

ዘውገኞች ህዝብን ከመከፋፈል ይልቅ የሁሉም መብት በእኩልነት በሚከበርበት ጉዳይ ላይ ቢያተኩሩ የእኔ ነው ለሚሉት ጨምሮ ለሁሉም ብሄረሰቦች ደህነነት ዋስተና ነው፡፡የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ወርክ ስራውን የጀመረው ኦሮሞን እና ኦሮሞነትን ብቸኛ አጀንዳ አድርጎ ነው፡፡ የኦሮሞ ዘውገኞች ፤ፊታውራሪወች፤ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ እና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ሚዲያውን በመጠቀም አብረን መሆን ካልቻልን ጥሩጎረቤት እንሆናለን በማለት የኦሮሞ የስደት መንግስት የማቋቋም፤ የነጻነት ቻርተር የማርቀቅ፤ የኦሮሚያ ካርታ የማዘጋጀት፤ የአብሲኒያ ኢምፓየር ወረራ በኦሮሞ የሀገር ውሰጥ ፍልሰት ወረራ ተተክቷል በማለት የኦሮሞን የበላይነት የማስፈን ስራ ጀምረው ነበር፡፡

ይህ የተሳሳተ ጉዞ ያሳሰባቸው ኦሮሞዎች አንድ ኦሮሞ መልሶ ለራሱ ጎረቤት አይሆንም ፤በኦሮሞ ደም እና ላብ የተገነባች ኢትዮጵያ መልሳ ለራሷ ጎረቤት አትሆንም ፤አንድ አካል ከራሱ አካል አይለይም ብለው ያስነሱት ተቃውሞ፤ የቄሮ እና የፋኖ ደምህ ደሜ ነው የጋራ ትግል፤ በኦሮሞ ዘውገኛ ሊህቃን እና በሌሎች መካከል በታሪክ እና ትርክት ልዩነት ላይ የተካሄደው የሚዲያ እና የብዕር ጦርነት የፈጠሩት ግፊት እና ጫና ተጀምሮ የነበረው ጉዞ ጋብ አለ፤ በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክም ላይ የተወሰነ ለውጥ ታዬ፡፡
የመጣውን ለውጥ ነጥቆ ወጣቱን ወደ ራሳቸው የዘውግ ፍላጎት ለማስጠጋት ከፍተኛ መሯሯጥ ይታያል፡፡

ኦሮሚያ ኢትዮጵያን የተካች ይመስል የኦሮሞ እንጅ ሌላው ችግር እና ፍላጎት የሌለው ይመስል በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ በደጀኔ ጉተማ እና በኢታና ሀብቴ መድረክ መሪነት በተለይም በፕሮፈሰር ህዝቅኤል ገቢሳ እና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ተደጋጋሚ ተሳታፊነት ቄሮ የለውጡ ባለቤት እንደሆነ የኦሮሞ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ እንደሆነ የኦሮሞ ጥያቄ ሲመለስ እና ፍላጎቱ ሲሟላ ችግሮች እንደሚወገዱ፤ የዶ/ር አብይ አህመድ ቅቡልነት እና የመንግስቱ ስኬታማነት የኦሮሞን ጥያቄ በመመለስ ብቃት እንደሚለካ፤ አፋን ኦሮሞ የስራ ቋንቋ መሆንን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፍላጎቶች ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ካልተሟሉ በማለት ከፍተኛ የማስፈራራት ዘመቻ እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱ የሚካሄደው በመድረክ መሪዎች በጥንቃቄ በተዘጋጁ ፤ በእቅድ እና ስሌት በተመረጡ የኦሮሞን ተረኛ የበላይነት አመላካች በሆኑ ልዩ ፍላጎቶች ላይ ነው፡፡ የተያዘው አቋም እና አካሄድ ምን ያህል አደገኛ፤ አስከፊ እና አስደንጋጭ እንደሚሆን ከወያኔ አመጣጥ እና አወዳደቅ መማር ይቻላል፡፡ የርቀት የሚዲያ መስኮት ታጋዮች ህዝቡን የሚለበልበው እሳት ቀርቶ ወላፈኑ አይደርስባቸውም ፡፡ ጸጋዬ አራርሳ የሚኒሊክን ሀውልት አፍርሱልኝ ከማለት ይልቅ ወደ አራዳ ጌወርጊስ ብቅ ብሎ ማፍራረሱን ቢሞክረው የአሳቱን እና የወላፈኑን ውጤት ወዲያውኑ ሊያገኘው ይችልነበር፡፡

ወያኔ አማራ ጨቋኝ ሌሎች ተጨቋኝ የሚል የፈጠራ ትርክት ተጠቅሞ ስልጣን ይዞ በሀገር እና ህዝብላይ ዘግናኝግፍእናበደልስላደረሰእንቢአልገዛምህዝባዊአመጽ የስልጣንእድሜውን ቀጠፈበት፡፡ የኦሮሞ የዘውግ ፊታውራሪዎችም አማራ ጨቋኝ ኦሮሞ ተጨቋኝ የሚል እንደ ወያኔ ብልጣብልጥ ትርክት ተጠቅመው ስልጣን ለመያዝ በከፍተኛ ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡ የስልጣን ጉጉት ስለሚያደነዝዝ ፤ የማሰብ አቅምን ስለሚሰልብ፤ ዘረኛ ስግብግብ እና እራስ ወዳድ ስለሚያደርግ ነው እንጅ የኦሮሞ ዘውገኞች እጣ ፈንታቸው እንደ ወያኔ እንደሚሆን ስተውት አይደለም፡፡

በፕሮፌሰር ህዝቅኤል አማራ ጨቋኝ ኦሮሞ ተጨቋኝ አቋም ላይ ከአቶ አቻምየለህ ጋር ውይይት ተደርጎ ነበር አቶ አቻምየለህ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ኦሮሞ ተጨቋኝ ለሚለው አቋሙ ተጠያቂው አማራ ሳይሆን በሚኒሊክ እና ከእኛ በላይ ኦሮሞ የለም ባሉት በንጉሰ ነገስት ተፈሪ መኮነን ጉዲሳ /ሃይለ ስላሴ/ዙሪያ አብረው ሲያማክሩ ሲወስኑ እና ሲያስወስኑ ነበር፡፡

ያላቸውን የኦሮሞ የሚሊተሪ እና የሲቪል ባለሰልጣኖች ናቸው በማለት ስምጠቅሶ ላቀረበው ማስረጃ አወያዩ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ተጠያቂ አማሮች ናቸው ለሚለው አቋሙያለውን ማስረጃ እንዲያቀርብ ሲጠይቀው ያቀረበውማስረጃሳይሆን
ከውይይቱ ጭብጥ የራቀ እና አቅጣጫ አስለዋጭ (diversion tactic) ኩነና ነው፡፡ ተጨባጭ ማስረጃ አቅረቦ ማሳመን ወይም የቀረበ ተጨባጭ ማስረጃን መቀበል ትልቅነት ሙያዊነት እና ሃላፊነት ነው በሚባልበት ዘመን ከዚህ ውጭ ሆኖ አሳሳች እና አደናጋሪ ትርክት ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
እነ HÍ= ጃዋር መሃመድ ዛሬ የያዙት ሃገራዊ እና ዲሞክራሲያዊ አቋም መልካም ስለሆነ ሊቀጥሉበት ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያደረገላቸው አቀባበል ለሚጠብቃቸው ሃላፊነት ትልቅ አደራ ነው፡፡

የኦሮሞሚዲያ ኔትወርክለምንየኦሮሞድምጽሆኖእንደተቋቋመለመረዳትአያስቸግርም ዛሬ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ በሀገር ውስጥ ቅርንጫፎች እንደሚከፍት፤ በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሚያሰራጭ በሃጂ ጃዋር መሃመድ ተገልጿል፡፡ ይህ እቅድ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን ከኦሮሞ ድምጽነት ወደ ሀገራዊ ድምጽነት ለማሸጋገር የታሰበ ይመስላል:: ይህ ከሆነ ከአደረጃጀት፤ ይዘት፤ ስርጭት፤ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ፤ የሰው ሃይል. . . ወዘተ ድረስ ከሚጠብቀው ሃላፊነት ጋር የተጣጣመ ለውጥ ይፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን በነበረበት የሚቀጥል ከሆነ Ó” ወደታላቁ ግብ SÉ[e” ›e†Ò] ÁÅ[ÑaM::

ዘውገኞች እና አንድነቶች በብሄርተኝነት እና uኢትዮጵያዊነት ላይየተፈለገውን ያህል ተቀራርበዋል ማለት አይቻልም፡፡ ዘውገኞች ኢትዮጵያዊነት ከጎላ ከብሄረሰቦች ማንንት ከቋንቋ፤ ከባህል እና እራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር ከተያያዙ መብቶች እና ነጻነቶች ላይ ጫና ያደርጋል፡፡ ክልልን ያሳጣል ፤የቋንቋ ፌዴሬሽንን ያፈርሳል የሚል ስጋት አላቸው፡፡ አንድነቶች በተጻራሪው የብሄሮችን መብት እና ነጻነት ስለሚቀበልእናስለሚያከብር የኢትዮጵያዊነት መጉላት ለብሄረሰቦች መብት እናነጻነት መጠናከር ተጨማሪ አቅም እና ጉልበት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ክልል የብሄረሰቦች እንጅ የነዋሪወች አይደለም የሚለው፤ የክልሉ ብሄር አባል ላልሆኑ ነዋሪዎች እኩል መብት እና ነጻነት የሚነፍገው፤ የእኛ እና የእናንተ ብሎ ኢትዮጵያን የተቀራመተው ፤የብሄሮችን የጋራ እሴት፤ ባህል፤ ታሪክ እና ማንነት ፤ ደምስሶ የጋራ ቤት ኢትዮጵያን ያሳጣው ግጭትን ደም መፋሰስን፤ ሰብዓዊ እና ማህበራዊ ቀውሰን ፤ያመጣው የቋነቋ ፌደሬሽን መሰረት የሆነው ብሄርተኝነት የሰላም እና የደህንንት የዲሞክራሲ እና ነጸነት፤የእድገት እና ብልጽግና፤ የአንድነት እና የእኩልነት እንቅፋት አድርጎ ይመለከተዋል፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው ለዘውገኞች እና ለአንድነቶች አለመቀራረብ ምክንያት የብሄርተኝነት እና የኢትዮጵያዊነት ያለመጣጣም ችግር ሳይሆን በዚህ ሰበብ የታዘለው ድብቅ የበላይነት እና የስልጣን ፍላጎት እንደሆነ ነው፡፡

ኢህአዴግ አስደምሬ በራሴ ቦይ ውስጥ አስገባለሁ ከሚለው ስሌት እንዲሁም ህብረብሄር ድርጅቶች ከጥቃቅን እና አነስተኛ የህብረት ስራ ማህበራት መሰል ፖለቲከኛነት ወጥተው ዘውገኞችን ከዳግማዊ ዘመነ መሳፍንት መሳፍንትነት ማቀብ ካልተቻለ የተጀመረውን የለውጥ ሂደትን አደናቅፎ፤ ኢትዮጵያን መልሶ ወደትርምስ እንድትገባ መፍቀድ ነው፡፡ ለውጤታማነቱ ለውጡን ያመጣው ሃይል ህጋዊ እና ስርዓታዊ ጫናውን ሊያጠናክር ይገባል፡፡

addisjember@yahoo.com

LEAVE A REPLY