አቶ ደመቀ መኮንን በአዴፓ /በአዴን መሪነት እንደሚቀጥሉ ተስማሙ

አቶ ደመቀ መኮንን በአዴፓ /በአዴን መሪነት እንደሚቀጥሉ ተስማሙ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ሰሞኑን የገዢው ኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተናጠል የሚያደርጉት ጠቅላላ ስብሰባዎች ዙሪያ አነጋጋሪ የሆነው የአቶ ደመቀ መኮንን ከብአዴን/አዴፖ የመሰናበት ጥያቄ ጉባኤው ሳይቀበለው በመቅረቱ አቶ ደመቀ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ላይ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል።

ጉባኤው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ከ13 የሰራ አስፈጻሚ አባላት 12 እንደሚመረጥና ከአቶ ደመቀ ዉጭ አዲስ ተመራጮችን በማካተት ዛሬ ጉባኤውን እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ጉባኤው አቶ ከሳ ተክለብርሃንን እና ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ አምባሳደር ስለሆኑና በሃገር ውስጥ ስለማይገኙ በሚል ምክንያት በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዳይካተቱ የተውሰነ  ሲሆን  የክልሉን ህዝብ በመሳደብና በማዋረድ በብዙሃኑ የተወገዙት አቶ አለምነው መኮንንን ጨምሮ ሌሎች አምስት ሰዎቸም በትምህርት ሰበብ ከ65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ እንዳይካተቱ ተወስኗል።

የተለያዩ አዳዲስ ውሳኔዎችን ያሳለፈው የአዴፖ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሲጠናቀቅ ከአቶ ደመቀ ሌላ 12ቱን ወሳኝ የድርጅቱን ሰዎች ይፋ በማድረግና የ65ቱን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም በመዘርዘር ይጠናቀቃል።

LEAVE A REPLY