/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/ :- ባለፉት አመታት በከፍተኛ የፖለቲካና የደህንነት ውጥረት የሚከበረው አመታዊው የኢሬቻ በአል ትላንት በከፍተኛ ድምቅት ተከብሮ ዋለ::
አመታዊው የምስጋና በአል የመንግስት ባለስልጣናት: አባ ገዳዎችና ከተለያዩ አካባቢ የመጡ የኦሮሞ ተወላጅ ኢተዮጵያዊያኖቸን ጨምሮ የልዩልዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች በተገኙበት በቢሸፍቱ /ደብረዘይት/ ከተማ ሲከበር ውሏል::
ክብረ በአሉን በማስመልክት የኦሮሚያ ክልል ርአሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው መላው ህብረተሰብ እና አባገዳዎች እንዲሁም ለጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ክብረ በአሉ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ከቆሙ ሁሉንም ነገር ማሳካት እንደሚችሉ የሚያሳይ መሆኑን ያወሱት አቶ ለማ ከየክልሎቹ የመጡ ብሀረሰቦች መሰባሰባቸው ልዩ ድምቀተ ሆኖ ማለፉን ጠቁመዋል።
አቶ ለማ መገርሳ በመግልጫቸው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አንድነታችንንና ሰላማችንን ለማወክ ለሚፈልጉ ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል ከማለታቸውም በተጨማሪ በዓሉ ሊከፋፍሉን ለሚፈልጉ፣ ትልቅ መልዕክት ማስተላለፉን ገልጸዋል።
በ2009/2016 ዓም የኢሬቻ በአልን ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡ ኢትዮጰያዊያን ላይ የመንግስት ታጣቂዎች በከፍቱት ተኩስ 55 ዜጎች መገድላችውን ህወሃት ይመራው የነብረው መንግስት ሲያምን ተቃዋሚዎችና አለም አቀፍ ተቅዋማት ግን የመቶዎች ህይወት መቀጨቱን መዘገባቸው ይታወሳል::