ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ

ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ።

ደኢህዴን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

2.አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

3. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ

4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

5. አቶ ተክለወለድ አጥናፉ

6. አቶ ሳኒ ረዲ

7. አቶ ታገሰ ጫፎ

8. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

9. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም

10. አቶ ደበበ አበራ

11. አቶ መኩሪያ ሀይሌ

12. አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ

13. አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ

14. አቶ ተመስገን ጥላሁን

15. አቶ ወዶ ኦጦ

16. አቶ ያዕቆብ ያላ

17. አቶ ሰለሞን ተስፋዬ

18. አቶ ፀጋዬ ማሞ

19. አቶ ንጋቱ ዳንሳ

20. አቶ አድማስ አንጎ

21. አቶ ኑረዲን ሀሰን

22. አቶ ሞሎካ ወንድሙ

23. አቶ አብቶ አልቶ ናቸው ከማእከላዊ ኮሚቴው በክብር የተሰናበቱት።

ከማእከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱት አባላት ከ17 እስክ 15 ዓመታት በተለያየ የሀላፊነት ደረጃ ያገለገሉ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባዔው በተጨማሪም ከድርጅቱ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አቶ ካሚል አህመድን በክብር አሰናብቷል።

እንዲሁም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ እስከ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በእግድ እንዲቆዩ አድርጓቸው የነበሩ አባላትንም ድርጅታዊ ጉባዔው አሰናብቷል።

በዚህም መሰረት፦

1. ወይዘሮ አማረች ኤርሚያስ

2. አቶ ሳሙኤል ደምሴ

3. ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል።

ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬው እለት የማእከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እንዲሁም የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ክትል ሊቀ መንበር ምርጫ በማድረግ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በበላይ ተስፋዬ

/ምንጭ ፡ – ፈና/

LEAVE A REPLY