ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሃይል ማዘናቸውን መጠቀም እንደሚገባቸው ተገለጸ

ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሃይል ማዘናቸውን መጠቀም እንደሚገባቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ባሳለፍነው ሳምንት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ያካሄዱትን ጠቅላላ ጉባኤ ፈጽመው ዛሬ ረቡዕ ወደሚጀምረው የኢህአዴግ ወሳኝ ጉባኤ የሚያመሩ ሲሆን አራቱም አባላት በውስጥ ባካሄዱት ውስብስብ ውይይት የድርጅታቸውን ስያሜ እና አርማ አሰከመቀየር የዘለቀ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።

ኦህዴድ መጠሪያውን እና አርማውን ጨምሮ ልዩ ልዩ ውስጥ ነቀል ለውጦችን አካቶ በአዲስ መንፈስ ወደፊት ሊያራምደው በሚችል መልኩ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

ደህዴን በሌላ በኩል ያልተሳካላቸውን የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን እና ሽፈራው ሽጉጤን  ያማከለ ባለስልጣናትን ያሰናበተ ሲሆን ወ/ሮ ኬሪያን የድርጅቱነ እንዲመሩ መርጧል በዚህም የመጀመሪያው በሴት የሚመራ የኢህአዴግ አባል ድርጅት አድርጎታል።

ህውሀት በሌላ በኩል አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት አምጥቼ ጉባኤየን አጠናቅቄያለሁ በማለት በቃል አቀባዩ  ጌታቸው ረዳ በኩል ይፋ ስታደርግ በመጥፎቱና በብዙ ህይወትና ሰዎችን በእስር ቤት በመሰቃየት የሚታወቀውን የቀድሞ የደህንነት ሹም ጌታቸው አሰፋን የሰራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አንዱ መደረጉ ይፋ ተደርጓል።

ዛሬ በሚጀመረው ጉባኤ ብዙ የተዘበራረቁ ሁኔታዎች የሚያስተናግድ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን ድርጅቱ መጻኢዉን ፈታኝ የፖለቲካ ውጥንቅጥ የሚፈታበትን ፍኖተ ካርታ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይሄ ጉባኤ ፈተና ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ነገ የሰጡት የፖለቲካ ተንታኝ ሀገሪቱ በጎሳ የፖለቲካ በተናጠችበትና በተለይ በጽንፈኞች ቀንበር የሚፈጸም ብሔር ተኮር መፈናቀል በየአካባቢው የሚስተዋልባቸው በተባረሩት ወቅት መሆኑ ፈተናውን እንደሚያባብሰው ጠቁመዋል።

በተለይ ዶ/ር አብይ ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ ቁርጠኝነት እንደሚጠበቅባቸው እና ይያዙትን የበላይነት ለማስጠበቅ ጠንካራ ክንዳቸውን ማሳየት ይገባቸዋል። ሲሉ አስተያየታቸውን በመቀጠል ከህወሃት ብቻ ሳይሆን ከጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎችም ከውስጣቸው እንደሚፈታተኗቸው በማጤን መንገዳቸውን ማጽዳት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በተለይም የኦነግ ጽንፈኞች ከህወሃት ጽንፈኞች ጋር በማበር ሊያደርሱ የሚችሉትን የፖለቲካ ትርምስ ከግምት ውስጥ በማስገባት በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ጥርጊያ ማመቻቸት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋነኛ ስልት መሆን ይገባዋል ሲሉ የፖለቲካ ተነታኙ ለኢትዮጵያ ነገ ድረገጽ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY