ህወሓት/ኢህአዴግ ያጠፋው የአማራ ህዝብ ብዛት ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ ብዛት ይበልጣል!

ህወሓት/ኢህአዴግ ያጠፋው የአማራ ህዝብ ብዛት ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ ብዛት ይበልጣል!

በእርግጥ በህወሓት ዘመን ተወልዶ በኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ እየታጠነ ያደገ ትውልድ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ከአማራ ሕዝብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጥ ሊመስለው ይችላል። እውነታው ግን ከዚህ ፍጹም የተለየ ነው። ለምሳሌ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየ10 አመቱ የሚያካሂደውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ዋቢ በማድረግ ብንመለከት እ.አ.አ. በ1984 (1977 ዓ.ም) በኦሮሞ እና አማራ ህዝብ መካከል ያለው ልዩነት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ነው። ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው በ1984 ዓ.ም (እ.አ.አ.) የኦሮሞ ህዝብ ብዛት 12.38 ሚሊዮን ሲሆን የአማራ ህዝብ ብዛት 12.05 ሚሊዮን ነው። ከአስር አመት በኋላ እ.አ.አ. በ1994 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት 17.08 ሚሊዮን ሲሆን የአማራ ህዝብ ደግሞ 16.01 ሚሊዮን ነበር።

ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን ከአደላደለ በኋላ እ.አ.አ. በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ ግን የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር በ8.28 ሚሊዮን ጨምሮ 25.36 ሚሊዮን መድረሱን ያመለክታል። በአንፃሩ የአማራ ህዝብ ብዛት ከአስር አመት በፊት ከነበረበት በ3.86 ሚሊዮን ጨምሮ ብቻ ጨምሮ 19.87 ሚሊዮን ደርሷል። እ.አ.አ. በ1994 ዓ.ም በኦሮሞና አማራ ህዝብ መካከል የነበረው ልዩነት 1.07 ሚሊዮን ሲሆን የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን ካደላደለ በኋላ እ.አ.አ. በ2007 ዓ.ም ባካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ በኦሮሞና አማራ ህዝብ መካከል ያለው ልዩነት ከአስር አመት በፊት ከነበረበት 1.07 ሚሊዮን በአመስት እጥፍ ጨምሮ 5.49 ሚሊዮን ሆኗል።

በአጠቃላይ እ.አ.አ. በ1984 ዓ.ም ከአጠቃላዩ የሀገሪቱ ሕዝብ መጠን የኦሮሞ ህዝብ ብዛት 29.1% ሲሆን የአማራ ሕዝብ ደግሞ 28.3% ነበር። ዛሬ ላይ ከጠቅላላ የሀገሪቱ ሕዝብ ብዛት ኦሮሞ 35% ሰሆን የአማራ ህዝብ ብዛት ደግሞ 27% ነው። በኦሮሞ ህዝብ ብዛት እና አማራ ህዝብ ብዛት መካከል ያለው ልዩነት እ.አ.አ. በ1984 ዓ.ም ከነበረበት 0.8% ዛሬ ላይ 8% ደርሷል። በሌላ አነጋገር ባለፉት ሁለት አስር አመታት የጠፋው የአማራ ህዝብ ብዛት ከትግራይ፥ ሶማሌ፥ ሲዳማ፥ ሃድያ፥ ጉራጌ ወይም አፋር ህዝብ ብዛት ይበልጣል።

/ስዩም ተሾመ/

LEAVE A REPLY