በወሎ ሰፈር ዛሬ እርስ በርስ በተፈጠረ ግጭት የ3 የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ

በወሎ ሰፈር ዛሬ እርስ በርስ በተፈጠረ ግጭት የ3 የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ

በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ እርስ በእርስ በተፈጠረ ግጭት የ3 የፌደራል ፖሊሶች ህይወት አለፈ። በግጭቱም 5 ፖሊሶች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

በስፍራው ግጭቱ የተከሰተውም አንድ የፌደራል ፖሊስ ከአቻ ባልደረቦቹ ጋር በፈጠረው አለመግባባት ተኩስ ከፍቶ ሁለት ፌደራል ፖሊስ በመግደሉ መሆኑን ኮማንደር ብርሃነ ቢሆን በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ቀድሞ ተኩስ የከፈተው የፖሊስ አባልም እጅ ባለመስጠቱ እርምጃ ተወስዶበት ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በግጭቱ በአካባቢው ባሉ ህብረተሰቦች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ጠቁመዋል፡፡

በአሁን ሰዓትም አካባቢው በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ኮማንደሩ ጠቁመዋል፡፡

/ምንጭ ፡  ኢቢሲ/

LEAVE A REPLY