ኦነግ (OLF) በአስቸኳይ ትጥቅ ይፍታ!! /ከሙሉቀን ገበየሁ/

ኦነግ (OLF) በአስቸኳይ ትጥቅ ይፍታ!! /ከሙሉቀን ገበየሁ/

ከ 27 አመታት መራራ ሰላማዊ የኢትዮጲያ ህዝብ ትግል ቦኋላ የትግሉ መንፈስ በ ኢሕአዲግ (EPRDF) ተብሎ በሚጠራው ግንባር ውስጥ ሰንጥቆ ገብቶ በተለይም በቀድሞ ስሙ ኦህዴድ (OPDO) እና ብአዴን (ANDM) አመራር አባላቶች ትግሉን ተቀላቅለው ለውጡን እውን በማድርጋቸው ባለፉት 6 ወራት በአገራችን የሚታየውን የዲሞክራሳዊ መንገድ ጅምር ለማየት ደርሰናል።

በዶ/ር አብይ አሕመድና በተለምዶ “Team Lemma” የሚባሉት አመራሮች ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጲያዊንትን ባጎላ አመራር አገራችን ተስፋ ያለባት አገር እንድትሆን አድርጓታል። ባልፉት ወራት የተደርጉት ዲሞክራሲያዊ እርምጃዎች ፍጥንትና የተገኙት ውጤቶች ብዞዎቻችንን ያስግርመ ነው። ይህ የሚያበርታታ እርምጃ በፅኑ የሚደግፍ ነው። ከተደርጉት መልካም እርምጃዎች አንዱ ነፍጥ/መሳርያ አንስተው የትጥቅ ትግል የሚያድርጉትና በመንግስት በሽብርትኛንት ተሰይመው የነበሩ የፖልቲካ ሃይሎችን በሰላማዊ አሕመድ ሃገራቸው ገብተው እንዲታገሉ መድርጉ ነው።

በይበልጥ የሚታወቁት ኦነግ (OLF)፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት (AG7) ፣ ኦነሌፍ (ONLF) እንዲሁም ሌሎችንም ይጨምራል። አብዛኛዎቹ በይፋ ጥሪውን ተቀብለናል ብለው፤ ይፋ ባልሆነ ስምምነት ከመንግስት ጋ አድርገው ወደ ሃገር ውስጥ በሰልፍና በደስታ ገብተዋል። የኢትዮጲያ ህዝብም የድርጅቶቹ ደጋፊዎች እንኳን ድህና መጣችሁ ብሎ በአደባባይ ተቀብሎቸዋል።

ዋና መሰርታዊ ጉዳይ በሰላሚዊ መንገድ ትግል እናደርጋልን ማለታቸው ሲሆን ወደ አገር ውስጥ የገቡት የታጠቁትን መሳርያ አስርክበው ወይም ከጥቅም ውጪ አደርገው፣ ሰራዊታቸውንም ወደ ሲቭልነት ለመቀየር ወታደራዊ ካንፕ አስግብተው እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ ካልሆነ ግን ትልቅ ስህተት፣ ጥፋት እንዲሁም ይህንን የፈቀዱ ወይም የተስማሙ የመንግስት ባለስልጣኖች የክህደት ተግባር ፈጽመዋል ማለት ነው። እውቅና ካለው የሃገሪቱ መንግስት ውጪ ማንም የፖለቲካ ፓርቲ ትጥቅ ከያዘ ሰላማዊ ትግሉን በመተው በመሳርያ ሃይል አላማውን ከማሳካት ውጪ ሌላ የሚያደርገው ተግባር አይኖርም።

የኢትዮጲያ ህዝብ ለ 27 አምታት ያደርገው ሰላምዊ ትግልና መሰአውትነት በሌሎች መሳርያ በታጠቁ ሃይሎች ሊነጠቅ በፍፁም አይገባም። በተለይም የተወሰነ ህዝብና ወገን ታሪካዊ ጠላቴ ነው ብሎ የተነሳ የፖለቲካ ሃይል ትጥቅ ይዞ ከተጠያቂንት ውጪ ያሰማረችውን ነፍጥ ያነግቡ ሰራዊቱ በህዝቡ ውስጥ መግባታቸው በጣም አሳሳቢ ነገር ነው። ታጣቂዎቹ መሳርያ አስረክበው በወታደራዊ ካንፕ መቀምጥ ሲኖርባችው ይህ ሳይደርግ ከሆነ እጅግ አስጊና ባስቸኩይ ሊስተካከል የሚገባው ነው። ይህንንም የፈቀዱ ሰውች እንዲሁም ይህ እንዳይደርግ ስምምንት ተድርጎ ከሆነም ስምምንቱን ያፈርሰው አካል በአስቸኳይ ሀገር በመክዳት ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል።

ሪፖርት ጋዜጣ በ 3rd October በዘገባው ዜና መሰረት እያንቀሳቀሰ ያለውን ጦሩን ትጥቅ እንዲያስፈታ፣ ወታደሮቹንም በአስቸኳይ መንግሥት ወዳዘጋጀው ካምፕ እንዲያስገባ ተጠየቀ፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት የገጠርና ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ በግል የማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ እንዳሠፈሩት የኦሮሞ ነጽነት ግንባር ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ስምምነት አክብሮ መንቀሳቀስ አለበት ብሏል። የኦነግ አመራር የሆኑት አቶ ቶሌራ አደባ በበኩላቸው፣ አሁንም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አሁንም አስታጥቆ ትጥቃቸውን ያልፈቱ የኦነግ ወታደሮች እንዳሉ አምነዋል፡ https://www.ethiopianreporter.com/article/13211 ከመንግስት ውጪ መሳርያ የታጠቀ ሃይል ተጠያቂነት ስለሌለበት የፈለገውን ሊያድርግ ይችላል። ሊመስርት የተደከመበትን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ገና ከጅምሩ ያደርቀዋል፣ ያጠፋዋል።

ሰዎች በሰላማዊ መንግድ በሃስብ የሚደርጉትን ትግል በመሳርያ ሃይል በማስፍራራት የራሱን አላማ ለማስፈጸመያ ያደርገውል። ጠላቴ ነው የሚለውን ሃይል ከመግደልና ከማጥፋት አይመልስም። ወደፊት የሚደርገውን ምርጫ መሳርያ ያነግበው ሃይል በፈለገው መስረት ህዝቡን ከማስገደደ አይታቀብም። በአገር ውስጥ የርስ በርስ ጦረነት ውስጥ ሊከትንም ይችላል። የኦሮሞ ነፃንት ግንባር (OLF) ትጥቅ ሳይፍታ ከነሰራዊቱ ህዝብ ውስጥ መግባቱ እጅግ አሳሳቢ ነው። ኦነግ (OLF) ያለው አማራጭ አንድ ነው። በሰላማዊ መንግድ ትግሉን ለመቀጠል፡ ትጥቁን ባስችኩይ መፍታት፣ ሰራዊቱንም ወደ ወታድሪዊ ካንፕ ገብተው የሰላማዊ ኑሮ ተሃድሶ ትምህርት ስልጥና ቀሰመው ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ ማድርግ። ከለበልዚያ ከሽብርትኛንት ከሚለው ስያሜና ድርጊት ውጪ አይሆንም።

ኦነግን (OLF) ወደ አገር ቤት እንዲገባ ለማግባባት ወደ አስመራ የሄዱ የመንግስት አካላት፣ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ በዛ ወቅት የተስማሙበትን ና የተፈራርሙትን ስምምንቶች በይፋ ለህዝብ ባስቸኳይ መገለጽ አለበት። የለውጡ ዋና ሞተር ተብለው የሚቆጠሩት አቶ ለማ መገርሳ ኦነግ (OLF) ጥትቁን ሳይፈታና ሰራዊቱን ካንፕ ሳይግባ አገር ቤት ህዝቡ ጋ እንዲገባ ታላቅ ስህተት ይፍጽማሉ ተብሎ አይጥበቅም። ሆኖም ግን ባስቸኳይ ስምምንቱና ከነፊርማው በይፋ ለህዝብ መገልጽ አለበት ። ዋናው ጉዳይ ግን ኦነግም (OLF) ሆነ ሌሎችም ነፍጥ አንስተው የነበሩ ውይም ያሉ ማንኛውም የፖለቲካ ሃይሎች ሁሉ ባስቸኳይ ትጥቅ ፈተው ሰራዊታቸውን ወደ ካንፕ ማስግባት አለባቸው። በአገራችን የተለያዩ ክፍል ለሚታየው ግድያና ብጥብጥ መሳርያ ያነግቡ ሃይሎች አስተዋጾ ትልቅ ነው።

የመንግስት መሰረታዊ ዋና ተግባሩ ህግ ና ስርአት ማስከብሩ ስልሆነ፡ የኢትዮጲያ መንግስት ይህ ጉዳይን ባስቸኳይ ስር ሳይሰድ መፍቴ መስጠት አለበት። የኢትዮጲያ ህዝብም በተለይም ወጣቱ ይህን አገራችን ላይ ያገኘነውን ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንቢያ ጅምር እድል በፍፁም እንድዳያመልጠን ፅኑ ትግል ያስፈልጋል። የኢትዮጲያ ልጆች ሁሉ በሰላምና በፍቅር መሰርታዊ የግልና የወል መብታቸው የተከበርበት፣ በህግ ፊት ሁሉም እኩል የሆኑበትን፤ ሁሉም ዜጋ ለ ትምህርት፣ ስራ፣ ሃብት ለማፍርት እክሉ እድል ያልበት፤ ደሃ የማይበደልበት፤ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ብቻ የሚያዝበት አገር ና ስርአትን ለመመሥርት እጅጉን እንድስራ አግዚሃቤርም ይርዳን።

LEAVE A REPLY