በሻሸመኔ ሰው ዘቅዝቀው አንጠልጥለው በመግደል ወንጀል የተያዙ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሻሸመኔ ሰው ዘቅዝቀው አንጠልጥለው በመግደል ወንጀል የተያዙ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

/Ethiopia nege News/:- በሻሸመኔ ከተማ ሰው አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በመስቀል ግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ 14 የሚሆኑ ግለሰቦች ላይ በተመሰረተ ክስ ተከሳሶች ፍርድ ቤት ቀረቡ::

ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም በሻሸመኔ አካባቢ ጃዋር መሀመድ በተገኘበት የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ በተፈጠረ ግርግር በጅምላ ፍርድ በዘግናኘ ሁኔታ ሰውን አንጠልጥሎ በመስቀል ወንጀል መጠርጠራቸውን የአቃቤ ህግ መዝገብ አስታውቀ።

ዛሬ በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ የፍርድ ቤት ውሎ ክቀረቡት ተከሳሾች ገመዲ ሹሚ በዳዶ፣ ጀዋሮ ሁሴን ዋቃዮ፣ አርገታ በሽር ቱሲ፣ ከድር ማሞ በቀታ፣ በረዲን ሁሴን ባዪሞ እና ዱሬሳ እና ተስፋዬ ሂርጳ ይገኙበታል።

ፍርድ ቤቱ የከሳሽ ተከሳሽ ቃል በማዳመጥ ለጥቅምት 5 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY