ልብ ያለው ልብ ያድርግ /አፈንዲ ሙተቂ/

ልብ ያለው ልብ ያድርግ /አፈንዲ ሙተቂ/

እውነታው ተደጋግሞ ይነገር!

# በሁለቱም ባንዲራዎች ላይ ያሉት ቀለማት ተመሳሳይ ናቸው። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ።

# ባለኦዳውን ባንዲራ “የኦነግ ባንዲራ” ብሎ መጥራት ስህተትም፣ ተንኮልም ነው። “የኦነግ ባንዲራ” የሚለውን አነጋገር ያጧጧፈው ወያኔ ነው።

# ባንዲራው በትክክለኛ ስሙ “የኦሮሞ ህዘብ ባንዲራ” ነው የሚባለው። ኦነግ እንኳ በኪነት ቡድኖቹ ባቀናበራቸው ዘፈኖች “የኦሮሞ ባንዲራ” ብሎ ነው የሚጠራው እንጂ የኔ ባንዲራ አይልም።

# ባንዲራው የሁሉም ኦሮሞዎች የጋራ ንብረት ነው። ከኦዴፓ እና ኦፌኮ ውጪ ያሉት የኦሮሞ ድርጅቶችም ባንዲራውን እንደ ትግል አርማ ይጠቀሙበታል።

# የኦሮሞ ባንዲራ በእድሜው ከኦነግ መፈጠር አስር ዓመት ያህል ይቀድማል። በመጀመሪያ ጠበቃ ኃይለማሪያም ገመዳ “ኦዳ” የኦሮሞ ህዝብ አንድነት፣ ታሪክና ባህል መለያ እንዲሆን አስተዋወቀው። የባንዲራውን ዲዛይን “ሙሐመድ ዑመር ቃዲ” በ1958 ገደማ ሰራው። እነ ኤሌሞ ቂልጡን የመሳሰሉ አርበኞች ደግሞ ባንዲራውን የኦሮሞ ህዝብ የነፃነት ትግል አርማ በማድረግ አፀደቁት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባንዲራው በስውርም ሆነ በግልጽ ለኦሮሞ ህዝብ ተዋወቀ። ኦሮሞዎችም በውዴታ ተቀበሉት።
—–
እንግዲህ ዋናው ጥያቄ “በሁለቱ ባንዲራዎች ላይ ያሉት ሶስት ቀለማት ለምን ተመሳሰሉ?” ነው። መልሱ ቀላል ነው።

ቀደምት የኦሮሞ አርበኞች የነፃነት ትግሉን ሲጀምሩ ዓላማቸው ኦሮሞን ከኢትዮጵያ መነጠል ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ ብሄራዊ መብቱ ተከብሮለት በኢትዮጵያ ውስጥ በእኩልነት እንዲኖር ማስቻል ነው። በመሆኑም በኦሮሞ ባንዲራ ላይ ያሉት ሶስት ቀለማት በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ካሉት ሶስት ቀለማት ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን ወሰኑ። የዚህ ውሳኔ መልእክትም “የትም አንሄድም፣ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነን” የሚል ነው።
—–
ከሁለቱም በኩል ያሉ ጽንፈኞች በባንዲራው ላይ ሲጣሉ አትስሟቸው። በዚህ ዘመን አርማን ተገን አድርጎ መባላት ጅልነት ነው።
—-
ሼር ያድርጉትና ለሌሎች ያድርሱት።

LEAVE A REPLY