የአፋር ክልል ገዢ ፓርቲ አብዴፓ ሥራ አስፈፃሚ በዝግ ስብሰባ እየተወያየ ነው

የአፋር ክልል ገዢ ፓርቲ አብዴፓ ሥራ አስፈፃሚ በዝግ ስብሰባ እየተወያየ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአፋር ክልልን የሚያስተዳድረው ፓርቲ አብዴፓ ሥራ አስፈፃሚ አባላት በዝግ ስብሰባ እየተወያየ መሆኑ ታውቋል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ እየተደረገ ባለው በዚህ ጉባዔ ከሰሞኑ በክልሉ አነጋጋሪ የሆነውን የፕሬዝዳንት ሀጂ ስዩም አወል ስልጣን መልቀቅ እልባት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ።

ክልሉ ከተንሠራፋበት የሙስና ችግር፣  ከፍተኛ የህወሀት ጥገኝነት እና አንድ አካባቢን ብቻ ያማከል የስልጣን ድልድል ሳቢያ ዱከሂና በመባል የሚጠሩት ወጣቶች ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲለቁ ግፊት ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወቃል።

በተለይ በትግራይ ክልል አዋሣኝ በሆነው በራህሌ አካባቢ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ ዱከሂና የመሬት ና የኢኮኖሚ ወረራን በመቃወም ከትግራይ እና አፋር ልዩ ኃይል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸው ጉዳዩን እንዳባባሰውና የክልሉ መሪ የሆኑት ሀጂ ስዩምም ስልጣን የማስረከብ አዝማሚያ እንዳሳዩ በቅርቡ ፕሬዝዳንቱ የክልሉን ወጣቶች ባወያዩበት ወቅት በስብሰባው የተካፈሉ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ነገ ምንጮች ጠቁመዋል ።

LEAVE A REPLY