የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፓርቲውን ሊ/መንበር ሀጂ ስዩም አወልን ከኃላፊነታቸው አነሳ

የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፓርቲውን ሊ/መንበር ሀጂ ስዩም አወልን ከኃላፊነታቸው አነሳ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/:- ትናንት 18/03/2011 ዓ/ም በተጠናቀቀው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድርና የፓርቲው ሊ/መንበር ሀጂ ስዩም አወል ከኃላፊነታቸው መነሣታቸውን የኢትይጵያ ነገ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።

ለቀናት በርስበርስ መወቃቀስና በክልሉ ወጣቶች ግፊት ሣቢያ ለሁለት ተሠንጥቆ ሲታመስ የቆየው ማዕከላዊ ኮሚቴ ከፌዴራል መንግስት ጋር ተመካክሮ ከተመለሠ ወዲህ ለአራት ቀናት ሲወያይ መሠንበቱ ይታወቃል።

በውይይቱ ማጠናቀቂያ በተደረገዉ ድምፅ-ውሣኔ ከ45 የማዕከላዊ ኮሚቴ ድምፅ ሠጪዎች “ይሰናበቱ” ለሚለዉ 42 ድምፆች ሲቆጠሩ፤ “አይሰናበቱ” 1ድምፅ አግኝቶ፤ 2 ሠዎች ድምፅ ከመሥጠት ተቆጥበው ስንብታቸው ባብላጫ ድምፅ መፅደቁን ምንጮች አክለው ገልፀዋል።

ዉሣኔውን በርካታ የአፋር ህዝብ መብት ተሟጋቾች መልካም ጅምር በሚል ያሞካሹት ሲሆን ይበልጥ ዘላቂ መረጋጋት እንዲመጣ ግን የቀጣይ ተሿሚዎች ማንነት ወሣኝ መሆኑን አስምረውበታል። ሊ/መንበሩን ጨምሮ ሌሎች ተተኪ አመራሮችን ለመሠየም በቅርቡ የሚደረገው የፓርቲው ሠባተኛ ጉባዔ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY