የኦሮሞ ዲሞክራሴያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና ኦዴግ ለውህደት የሚረዳቸውን የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

የኦሮሞ ዲሞክራሴያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና ኦዴግ ለውህደት የሚረዳቸውን የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/:- የቀድሞው ኦህዴድ እና ከኦነግ በርካታ አመራሮችን ይዞ የተለየው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ በጋራ ለመወዳደር የሚያስችላቸዉን ውህደት እውን ለማድረግ ወሣኝ የሆነውን የመግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸው ተገለጸ።

በኦዴፓ በበኩል ስምምነቱን የፈረሙት የፓርቲው ም/ሊ/መንበር ና የኦሮሞ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሣ ሲሆኑ በኦዴግ በኩል ደግሞ ኦነግን ለረዥም ጊዜ ሲመሩ የነበሩትና ባለመግባባት ከግንባሩ በመለየት ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን መስርተው የሚመሩት አቶ ሌንጮ ለታ መሆናቸው ታውቋል።

መጪው ምርጫ በተቃረበበት በዚህ ሠዐት የፖለቲካ ድርጅቶች ለተፎካካሪነት የሚያበቃ የተጠናከረ ቁመና እንዲኖራቸው በውህደት ቁጥራቸውን መቀነስና ጥንካሬያቸውን መጨመር እንደሚገባቸው ብዙዎች ይስማሙበታል። ከዚህ አንፃር የሁለቱ ድርጅቶች መዋሀድ ለሌሎች ፋና ወጊ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ አዴፓ እና የአማራ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መዋሀዳቸው ይታወሣል።

LEAVE A REPLY