ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት
ዳኛው እነ ጎሃ አፅብሃ ብሎ በተራ ቁጥር ተጠርጣሪዎችን መጥራት ጀመሩ
1ኛ ተከሳሽ
.
.
.
13ኛ ተከሳሽ ረ/ኢር ምንላርግልህ
… አቤት
14ኛ ተከሳሽ ረ/ኢ/ር ርዕሶም
…አቤት
15ኛ ተካሳሽ ዋ/ሳጅን እቴነሽ
…አቤት
ምን ልበላችሁ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ ደስታ አለማመን አሸናፊነት ብቻ ሁሉም ተቀላቀሉብኝ
የትናንት መርማሪዬ ሰዳቢዬ እና ገራፊዬን እኔና ጓደኞቼን አቁሞበት የነበረበት የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ቆሞ አይኑን እያቁለጨለጨ ሳየው የእግዚአብሄርን ኤልሻዳይነት እያሰብኩ እንባ ተናነቀኝ
ምንላርግልህ ትናንት እናቴን ማዘር እንግዲህ መጠንከር ነው በዚህ እድሜዋ ሳታገባ ሳትወልድ እድሜዋን በማረሚያ ቤት በማሳለፏ አዝናለሁ ቀድሞ ነበር መምከር አሁን ማልቀስ ምንም አያመጣም በርቱ በማለት ሲዘባበትባት ነበር
በህይወቴ ከምንላርግልህ ክፋት የማረሳው አንድ ቀን በለሊት አስጠራኝ ደሞ ምን ሊሉኝ ነው ብዬ ቢሮ ገባሁ
ቁጭ በይ አለኝ በቁጣ ቁጭ አልኩ
ወ/ሮ አልማዝ(አያቴን) ምንሽ ናቸው? አለኝ
ግራ በመጋባት ስሜት እንዴ እናቴ ናታ አልኩት
ረጅም ሳቅ በነገርሽ ላይ እናትሽ አንቺን ወልዳ ነው የሞተችው ስለማታውቂያት ነው ወ/ሮ አልማዝ አያትሽ ናቸው አለኝ… እና? አልኩት
እስከዛሬ ደብቀውሽ ስለኖርሽ ልንገርሽ ብዬ ነው አለኝ እየሳቀ…
በጣም ነው የተናደድኩት በቃ ለዚህ ነበር የጠራኝ በሱ ቤት የናቴን መሞት እኔ አላውቅም አሁን ነግሮኝ ለቅሶ ሊያስቀምጠኝ ነበር ይህን አረመኔ ነው ዛሬ አንገቱን ደፍቶ ተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ቆሞ ሲቅለሰለስ ያየሁት
ግዜ ደጉ ከሳሽ እና ተከሳሽ ቦታ አቀያይሮን እየታዘብን ነው
ለማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ትናንት በጠየቀው መሰረት ችሎቱ እስከዛሬ ፖሊስ የሰራቸውን ምርመራዎች በአግባቡ ተመልክተን ለምርመራ የተጠየቀው ቀን አስፈላጊ መሆኑን ስላመነበት ፈቅደናል በማለት ለታህሳስ 3/2011 ከሰዓት 8 ሰዓት ተቀጥሯል